የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በመላው ሀገራችን የተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል።

ግብረ-ኃይሉ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ፣ የአዝማሚያ ትንተና በማካሄድ፣ ተጋላጭ ቦታዎችንና አካባቢዎችን ለይቶ በቅድመ መከላከል ስራው ላይ በርካታ የሰው ኃይል በማሰማራት ከህዝቡ፣ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶችና ከበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረገው ለመላው ህዝብና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም ለበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴዎችና ለወጣቶች ግብረ ኃይሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

ከህብረተሰቡና ከበዓል አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋር በመቀናጀት የተሰጣቸውን ግዳጅ በሚገባ ለተወጡት የፀጥታና ደህንነት ኃይሎችም ግብረ-ኃይሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

የሀገራችን ጠላቶችና እነርሱ የሚመራቿው አሸባሪዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በደህንነታችን ላይ አደጋ ለማድረስ ስለሚጥሩ ህብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ እያሳየ ያለውን ቀና ትብብር ወደፊት በሚከበሩ ሌሎች ህዝባዊና ሐይማኖታዊ በዓላት ላይም አጠናክሮ እንዲቀጥል የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አስተላልፏል።