ወደ ቴክኖሎጂ የሚደረገው ሽግግር የሳይበር ደህንነትን ታሳቢ ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

 

2ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ከክልልና ከተማ መስተዳድር ለመጡ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

በዛሬው መርሃ ግብር የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ ወደ ቴክኖሎጂ የምናደረገው ሽግግር የሳይበር ደህንነትን ታሳቢ በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

"ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ካልተላበስን ደህንነትን ማረጋገጥ አዳጋች ነው" ያሉት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ሙያተኞችን ማሰልጠን፣ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት እና ቴክኖሎጂ መታጠቅ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የክልልና ከተማ መስተዳድሮች ቴክኖሎጂ ከመታጠቅ ባለፈም ህብረተሰቡን ማስተማር አንዱ ዋነኛ ተግባራቸው አድርገው ሊሠሩ እንደሚገባም ም/ዋና ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

በኢመደኤ የሳይበር ደህንነት ባለሙያ አቶ ገዳሙ ገ/ኢየሱስ በዛሬው ዕለት ለተገኙ ተሳታፊዎች በሳይበር ምንነትና ባህሪያት፣ በሳይበር ጥቃት፣ በሳይበር ደህንነት ሥጋቶች፣ ሳይበር በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ ያመጣው መልካም እና አሉታዊ አጋጣሚዎች እንዲሁም በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ተቋማት ምን እንደሚጠበቁ ገለጻ አድርገዋል፡፡

"የሳይበር ደህንነት የጋራ ኃላፊነት! እንወቅ፣ እንጠንቀቅ!" በሚል መሪ ቃል 2ኛው በሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በኢመደኤ አዘጋጅነት እየተከበረ ይገኛል፡፡