የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ ኢመደአን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሃሙድ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ጎበኙ። በእለቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለፕሬዝዳንቱና ለልዑካን ቡድናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ለእንግዶቹ አስጎብኝተዋል፡፡

የሶማሌው ፕሬዝዳንት ዛሬ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ በጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በቆይታቸውም በሁለትዮሽ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ምክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።