በሳይበር ምህዳሩ ላይ ራስን ከማንነት ስርቆት የምንከላከልባቸው መንገዶች የትኞች ናቸው?
በሳይበር ምህዳሩ ላይ ራስን ከማንነት ስርቆት የምንከላከልባቸው መንገዶች የትኞች ናቸው?
በሳይበር አለም ከሚፈፀሙ የሳይበር ጥቃቶች መካከል አንዱ የሆነው የማንነት ስርቆት (identity theft) ነው፡፡ይህ የጥቃት አይነት የሳይበር ጥቃት በማሀበረሰቡ ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግሮችንና ጫናዎችን ያስከትላሉ፡፡
ማንነትን ተገን ተደርገዉ ከሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች ራስን ለመከላከል ሊወሰዱ ከሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን መተግበር ወሳኝ ነዉ።
የምንጠቀመውን የበይነ-መረብ ፕሮቶኮል (IP address) ደህንነት ማረጋገጥ፤
በምንጠቀማቸው የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎቶች ላይ የሁለት ወገን
ማረገጋጫን (two factor authentication ) ተግባራዊ ማድረግ ፤
የፋይናንስ ክሬዲት ሪፖርቲንግ አገልግሎት መመዝገብና መጠቀም፤
የህዝብ ዋይ ፋይና ሌሎች ነፃ በይነመረብ (internet) አገልግሎት መስጫ አለመጠቀም፤
ጠንካራና በቀላሉ የማይገመት የይለፍ-ቃል መጠቀም (password) መጠቀም፤
የምንጠቀመውን ድረ-ገጽ(website) አድራሻ ትክክለኛነት ማረጋገጥ ወይም Uniform resource locater (URL) ደህንነትና ትክክለኛ የድረገጽ ፕሮቶኮል እየተጠቀምን መሆኑን ማረጋገጥ ፤
የምንጠቀማቸውን የማህበራዊ ሚዲያዎች ግላዊነት( privacy) ወይም ደህንነት ማረጋገጥ፤
የባንክ አካውንት ዶክመንቶችና ሌሎች ጠቃሚ የግል መረጃዎችን መጠበቅ፤
በተለያዩ አዳዲስ ድረ-ገጾች ላይ መረጃዎችንና ሊንኮችን ለመክፈት የግል መረጃዎችን ሲጠየቁ መረጃዎችን ከመስጠት መቆጠብ፤
ሌሎች ማንዋል መረጃዎቻችንን ለምሳሌ፡-የትምህርት ማስረጃዎች፣ የነዋሪነት መታዎቂያና የተለያዩ የግል መረጃዎችን መጠበቅ ከጠፉ ደግሞ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማደረግ በቶሎ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።