የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሜጀር ጀነራል ዶ/ር አሕመድ ናስር አል ራኢሲ በኢመደአ የስራ ጉብኝት አካሄዱ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (INTERPOL) ፕሬዝዳንት ሜጀር ጀነራል ዶ/ር አሕመድ ናስር አል ራኢሲን በኢመደአ በመገኘት ተቋሙ እየሰራቸዉ ያሉ የስራ እንቅስቃሴዎችን ጎብኝተዋል።

በስራ ጉብኝታቸዉ ወቅት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ለፕሬዝዳንቱ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የኢትዮጵያን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሰዉ ሃይል ልማት፣ የቴክኖሎጂ ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚረዱ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ምርቶች እንዲሁም ወቅቱን የዋጁ የአሰራር ስርዓቶች ትግበራ ዙሪያ ገለጻ አቅርበዋል።

የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሜጀር ጀነራል ዶ/ር በጉብኝታቸዉ ኢመደአ የሳይበር ደህንነት አቅምን በመገንባት ረገድ የመሪነት ሚናን የመጫወት አቅም እንዳለዉ ማየታቸዉን አንስተዉ በተለይ በታዳጊ ልጆችና የቴክኖሎጂ ባለቤት ለመሆን እየተሰራ ያለዉ ስራ ምሳሌ የሚሆን መሆኑን ጠቁመዋል።

በዉይይቱ ሁለቱ ተቋማት ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ የሳይበር ወንጀሎችን ለመከላከል፣ ጠንካራ የሆነ የመረጃ ልውውጥ ስርዓትን ለማጠናከር፤ የሳይበር ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል የዲጂታል ፎረንሲክ እና የሰው ኃይል አቅምን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተመካክረዋል።

Publicador de continguts


የቅርብ ዜናዎች