የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ሀገርን ከተለዋዋጭ የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችል አቅም ገንብቷል-የፌደራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአተለዋዋጭ የሆኑ የሳይበር ጥቃቶችን በብቃት በመመከት የሀገርን ጥቅም ማስከበር የሚያስችል የተሟላ አቅም መፍጠሩን የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) 2016 በጀት ዓመት የመንግሥት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም በተገመገመበት ወቅት የፌዴራል ተቋማት የሱፐርቪዥን ቡድን ተቋቁሞ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ አቅጣጫ ማስቀመጣቸው ይታወሳል።

በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚመራው የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና መሥሪያ ቤት ተገኝቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ የሱፐርቪዥን ቡድኑን በመቀበል አስተዳደሩ ሐገራዊ የሳይበር ደህንነትን እና ሉዓላዊነትን ከማስጠበቅ አኳያ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን ገለጻ አድርገዋል፡፡

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የአስተዳደሩን 9 ወራት እቅድ አፈጻጸም ለሱፐርቪዥን ቡድኑ አቅርበዋል፡፡ በዚህም ሐገራዊ የሳይበር ደህንነት በማስጠበቅ፣ ሐገር በቀል የሳይበር ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን በማረጋገጥ፣ በመሰረተ ልማት፣ በተቋም አደረጃጀት፣ በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በማልማት እንዲሁም ሌሎች ተቋሙ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን ለሱፐርቪዥን ቡድኑ ገለጻ አድርገዋል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪ ዘሪሁን ከበደ በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ የሳይበር ጥቃትን መከላከል የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አቅም እየገነባች መሆኑን በመስክ ምልከታው እንደተረዱ ገልጸዋል።

በተለይም ተለዋዋጭ የሆነውን የሳይበር ጥቃት መመከት የሚያስችሉ፣ ዘመኑ የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች በመዘርጋትና በሰው ኃይል ዘርፍ የተሰሩ ተግባራት የሚበረታቱ መሆኑን አንስተዋል።

አስተዳደሩ በቀጣይም ያሉትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል ክፍተቶችን እያረመ ሀገራዊ ተልዕኮውን በአግባቡ እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ በበኩላቸው የሳይበር ጥቃት ሳይፈጸም የመከላከልና ጥቃት ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም መገንባቱን ገልጸዋል።

የቁልፍ ተቋማትን ደህንነት ማስጠበቅ፣ ቴክኖሎጂዎችን በአገር ውስጥ የማልማት፣ የስጋት ዳሰሳ መስራትና ሌሎች የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸውም አስረድተዋል።

/ ትዕግስት አያይዘው እንደገለጹት ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ ቁልፍ በሆኑ ተቋማት ላይ 24/7 የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ተልዕኮ እየተወጣን ነው ሲሉ ለሱፐርቪዥን ቡድኑ አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የሳይበር ጥቃትን የመከላከል ስራ የሁሉንም ተቋማት ጥረትና የህብረተሰቡን የሳይበር ግንዛቤ ማሳደግ የሚፈልግ በመሆኑ ባለድርሻ አካላት አብረው ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ በበኩላቸው እንደገለጹት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ምህዳሩ የሚያስተናግደው የጥቃት ዓይነትና መጠን እየጨመረ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያም ይህንን ታሳቢ በማድረግ የሳይበር ጥቃትን በአግባቡ ለመመከት በቴክኖሎጂና በሰው ኃይል አስፈላጊውን አደረጃጀት በመገንባት የሁልጊዜም ዝግጁነት መፍጠሯን ገልጸዋል።

Publicador de continguts


የቅርብ ዜናዎች