የአዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢመደአ የስራ ጉብኝት አደረጉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የአዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጅባት አለምነህና ሌሎች የአክሲዮን ማህበሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) የስራ ጉብኝት አደረጉ።

የጉብኝቱ ዓለማ በቀጣይ ኢመደአ እና የአዋሽ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር በጋራ መስራት የሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ ለመምከርና ልምድ ለመቅሰም ታሳቢ ያደረገ ነዉ።

በጉብኝቱ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ወ/ሮ አስቴር ዳዊትና አቶ ሀኒባል ለማ የተገኙ ሲሆን ኢመደአ ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት እና የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየሰራቸዉ ስላሉ ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከጉብኝቱ በኋላም ሁለቱ ተቋማት በቀጣይ ሊሰሩባቸዉ በሚችሉባቸዉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል።

Asset-Herausgeber


የቅርብ ዜናዎች