የቁልፍ መሰረተ ልማት ደህንነትን በመጠበቅ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ንቅናቄ መፈጠሩ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አዘጋጅነት ከጥቅምት 1 እስከ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የተካሄደው 5ተኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በስኬት መጠናቀቁን የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ገለጹ፡፡ የወሩን መጠናቀቅ አስመልክቶ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡ በዚህም የሳይበር ደህንነት ወር ከተዘጋጀበት ዓላማ አኳያ ግቡን የመታ እንደነበር ም/ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በ5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በዋናነት የሀገራችንን ቁልፍ መሰረተ ልማት እና መሰረተ ልማቱን የሚያስተዳድሩ ተቋማትን የሳይበር ደህንነት በመጠበቅ የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ንቅናቄ መፈጠሩን አቶ ዳንኤል ጉታ ተናግረዋል፡፡ የወሩ ንቅናቄ ዋና አላማ የተቋማትንና የዜጎችን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ንቅናቄን በማካሄድ የዲጂታል ሉዓላዊነታችንንና ብሄራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ የሚደረግ ጥረትን መደገፍ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ተቋማትንና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የሳይበር ጥቃት መከላከል አቅምን ለማሳደግ የሚያስችሉ ምክክሮችና የውይይት መድረኮች መደረጋቸውን አቶ ዳንኤል ጉታ ገልጸዋል፡፡

5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር መጠናቀቅን አስመልክቶ ጥቅል ሪፖርት በኢመደአ የኮሚዩኒኬሽና ሳይበር ደህንነት ባሕል ግንባታ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ኃይሉ ቀርቧል፡፡ ዳይሬክተሩ በሪፖርታቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡

• በ5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አራት ዋና ዋና መድረኮች ተካሂደዋል፤ እነዚህም

1. “የቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደህንነት ለሀገር ሉዓላዊነት” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ መሰረት ያደረገና ቁልፍ መሰረተ ልማትን የሚያስተዳድሩ የመንግስትና የግል ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት፣ የዘርፉ ማህበራት ተወካዮችን ያሳተፈ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሂዷል፤

2. በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ ጸድቆ ተግባራዊ በሆነው “ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ” ከተለያዩ ቁልፍ ተቋማትና ሚኒስቴር መ/ቤቶች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ምክክር ተደርጓል፤ በዚህም ፖሊሲውን ወደመሬት ለማውረድና ለመተግበር የሚያስችሉ ምክክሮች ከመደረጋቸውም ባለፈ ለብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ፎረም ምስረታ መደላድል የሚፈጥሩ ጭብጦች ተይዘዉበታል፤

3. “የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ለሀገራዊ የሳይበር ደህንነት የሚጫወተዉ ሚና” በሚል ርዕስ የቪዲዮ ኮንፍረንስ የተካሄደ ሲሆን በዚህም ከአራት ሺ በላይ (4,000) በሀገራችን ከሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተዉጣጡ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአካዳሚክ ማኅበረሰብ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፤

4. “በዲጂታል ኢኮኖሚ ጉዞ የሳይበር ደህንነትና የዲጂታል መታወቅያ ሚና” በሚል ርዕስ የሁሉም ክልል እንዲሁም የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የኢኖቨኤሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በድሬዳዋ ከተማ ተካሂዷል። በዉይይቱም ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚደረገዉ ጉዞ ግቡን እንዲመታ የሳይበር ደህንነት እና የዲጂታል መታወቂያ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

• በወሩ በተካሄዱ ኮንፈረንሶችና የአዉደ ርዕይ መርሃ ግብሮች ከሁለት መቶ ሦስት (203) ተቋማት የተዉጣጡ ከአራት ሺ አምስት መቶ በላይ (4,500) ሰዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

• 5ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር አስመልክቶ የማኅበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ሊያጎለብቱ የሚችሉ የአጭር ቪዲዮ ዉድድሮች ተካሂደዋል፤ በውድድሩም 47 አጫጭር ቪዲዮዎች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ ቪዲዮዎች የሁለት መቶ ሺ፣ የመቶ ሺ እና የሃምሳ ሺ ብር ሽልማት እንደ ቅደም ተከተላቸው ተበርክቶላቸዋል፡፡

• የተቋማትን እና የዜጎችን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ሊያጎለብቱ የሚችሉ በርካታ የሚዲያ ንቅናቄ ሥራዎች ወሩን ሙሉ በስፋት ተሰርተዋል፤

• በአጠቃላይ በ5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በተለያየ መልኩ በተሰራ ንቅናቄ ሃምሳ ሦስት ሚሊዮን (53 ሚሊዮን) ያህል ዜጎች ተደራሽ ተደርገዋል፡፡

Asset-Herausgeber


የቅርብ ዜናዎች