የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገነባውን አዲስ ዌብ ፖርታል አስረከበ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የገነባው አዲስ ዌብ ፖርታል በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ ጀመረ፡፡ በ7 ቋንቋዎች አገልግሎት የሚሰጠው ድረ-ገጹ መረጃን በፍጥነት፣ በጥራትና በአስተማማኝ ደህንነት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችል የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል። አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ "የአራተኛ መንግስትነት" ሃላፊነቱን በአግባቡ ይወጣ ዘንድ ኢመደአ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹ ሲሆን፤ አዲሱ ዌብ ፖርታል ለበይነመረብ ጥቃት ፣ ለኮምፒውተር ቫይረስ እና ለመረጃ መንታፊዎች እንዳይጋለጥ አስፈላጊ የደህንነት መስፈርቶች እንዲሟሉለት መደረጉንም ገልጸዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት የትውልዱ ድምፅ የመሆን አላማ ያላቸው ተዓማኒ መረጃዎችን በሁሉም የሚዲያ አግባቦች ለመላው ዓለም ተደራሽ እያደረገ የሚገኘው አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስርጭት አድማሱን ከፍ ለማድረግ አዲሱ ዌብ ፖርታል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

Asset-Herausgeber


የቅርብ ዜናዎች