አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8 ) በኢመደአ ተከበረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8) የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራሮችና  አባላት በተገኙበት በተለያዩ መርሃ ግብሮች  በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የአስተዳደሩን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት የኢመደአ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ማሞ እንዳሉት፤ በተቋማችን አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ስናከብር የሴቶች እኩልነት የሚሰፍንበት ተፈጥሮአዊ እና  ሰው ሰራሽ ልዮነቶች ሳያግዳቸው ሴቶች ለጋራ ጉዳያቸው የጋራ ድምጻቸውን የሚያሰሙበት፣ ልምዶቻቸውን የሚለዋወጡበት፣ የሚማማሩበት እና የሚተጋገዙበትን እድል እና ትስስር ለመፍጠር በማሰብ  ነው ብለዋል፡፡

እንደ ተቋም “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” ስንል በተሰማራንበት የሳይበር ደህንነት ምህዳር  የሴቶችን ተሳታፊነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ከሁሉም የተቋሙ ማህበረሰብ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን በማስገንዘብ ነው ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አለም አቀፉን የሴቶች ቀን ስናከብር በየአመቱ ቁጥርን ከመጥራት ባለፈ ሴቶች በተሰማሩበት መስክ የላቀ ሚና እንዲጫወቱ ሁላችንም የበኩላችንን ሚና መጫወት እንደሚኖርብን በመገንዘብ ነው፡፡ በቀጣይም ሴቶች ያላቸውን አቅም በማውጣት እንደ ሀገር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን እውን እንዲሆን  ሴቶችን በጥናትና ምርምር ዘርፍ  በማሳተፍ አንደ ተቋም የሚጠበቅብንን  ሀላፊነት እንወጣለን ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት የህይወት ተሞክሯቸውን ያካፈሉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ክብርት  ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ሴቶች በተሰማሩበት የስራ መስክ ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች እጅ ሳይሰጡ ራሳቸውን ለማብቃት ያለመታከት ከሰሩ መድረስ ከሚፈልጉበት የስኬት ደረጃ ለመድረስ የሚያግዳቸው ነገር እንደ ሌለ  ከህይወት ተሞክራቸው በመነሳት ልምዳቸውን አካፍለዋል ፡፡

በሌላም በኩል በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች እና የህግ ጥበቃ አንዲሁም ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ  ተግዳሮቶች ዙሪያ የህግ ባለሞያና የሴቶችና የስርአተ ጾታ ከፍተኛ በለሞያ በሆኑት ተጋባዥ እንግዳ ወ/ሮ ሜሮን  አራጋው  ገለጻ የቀረበ ሲሆን፤ ባለሞያዋ በገለጻቸው እንዳሉት ኢመደአ በሳይበር ደህንነት ላይ እንደሚሰራ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋም  የሴት ሰራተኞች ወደ ቴክኖሎጂ መስክ ተሳትፏቸው እንዲጨምር እና የውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲኖራቸው  ምቹ የስራ ከባቢ ከመፍጠር አንጻር እየተሰሩ ያሉ አበረታች ስራዎች መኖራቸው ይበል የሚያሰብልና ተጠናክሮ መቀጠልም  ያለበት ተግባር  ነው ብለዋል፡፡

በኢመደአ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዲቪዥን ሃላፊ ወ/ሮ አበራሽ ሱላሞ በበኩላቸው  እለቱን አስመልክተው ለመላው ሴት ኢትዮጵያውያን እና የአስተዳደሩ አባላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፤  የኢንፎርሜሽ መረብ ደህንነት አስተዳደር በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ሁለንተናዊ አቅም ለማጎልበትና ለማብቃት በሚሰራቸው ሥራዎች  በተለያየ መልኩ ድጋፍ ላደረጉ አካላት እወቅና ሰጥተዋል፡፡

በእለቱ ከተቋሙ አባላት 1% ከደሞዝ በሚቆረጥ ድጋፍ እየተረዱ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ዘጋቢ ፊልም ለእይታ በቅቷል፡፡

አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ሴቶችን እናብቃ ፤ ልማትና ሰላምን እናገጋጥ” በሚል መሪ ቃል በአለማችን ለ 113ኛ ጊዜ  በሀገራችን ደግሞ ለ 48 ጊዜ እተከበረ ይገኛል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች