የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ሲንቄ ባንክ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና ሲንቄ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ስምምነቱ በዋናነት የባንኩን የሳይበር ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡ ስምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬከተር / ትዕግስት ሃሚድ እና የሲንቄ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ንዋይ መገርሳ ፈርመዋል፡፡   

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬከተር / ትዕግስት ሃሚድ በፊርማ ፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ኢመደአ የሐገሪቱን ቁልፍ መሰረተ ልማት የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ዋና ተልዕኮው መሆኑን ገልጸው፤ በዚህም የፋይናንስ ዘርፉን የሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ሥራዎችን ከፋይናንስ ተቋማት ጋር እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ከሲንቄ ባንክ ጋር የተደረገው የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትም የባንኩን አጠቃላይ የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡  

የሲንቄ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ንዋይ መገርሳ በበኩላቸው፤ ባንኩ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር በጋራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፤ አሁን ላይ ይህንን ግንኙነት በተደራጀና ቅርጽ ባለው መልኩ በመምራት የባንኩን የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሰረተ ልማት ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችሉ አቅሞችን ለመጠቀምና በጋራ ለመስራት ስምምነቱ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት ወደሥራ ለማስገባትና ለመፈጸም በትኩረት እንደሚሰራና ለዚህም በሁለቱም ተቋማት ሃላፊዎች ያለው ቁርጠኝነት ከፍተኛ እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች