የናይጄሪያ መከላከያ ኃይል ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሜጀር ጄኔራል ዳሂሩ ሳኑሲ የተመራ የናይጄሪያ መከላከያ ኃይል ሪሶርስ ማዕከል (Nigerian Army Resources Center) ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኘ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት በማረጋገጥ በኩል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እና በአሰራር ስርአት እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎችን አስጎብኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነት እና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የሚያስችል ብቁና ዘመናዊ ተቋም መገንባት መቻሏን ልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በዲፕሎማሲው መስክ ጥብቅ ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን የገለጹት ልዑካኑ፤ በሳይበር ደህንነት መስክም በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ለመስራት የሚችሉባቸው በርካታ መስኮች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የአፍሪካን የተሟላ ብልጽግና ማረጋገጥ የሚቻለው ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ሲቻል እንደሆነ ያነሱት ልዑካኑ፤ በዚህ ረገድ በሁለቱ ሀገራትም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሳይበር ደህንነት ተቋማት መካከል ስትራቴጂካዊ ትብብርና ቅንጅት በመፍጠር ለአሕጉራዊ የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች