የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በሳይበር መከላከል ዙሪያ 30 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ አስመርቋል

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንዔል ጉታ የዛሬዉ ምርቃት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና በኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት መካከል ያለዉ ትብብርና አጋርነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።

ሰልጣኞች በኢመደአ በነበራቸዉ ቆይታም ስለ ረቂቅ የሳይበር ጥቃት ዓይነቶች፣ መከላከያ ስልቶ፣ የጥቃት ማክሸፊያ መሳሪያዎችን አጠቃቀምና ቴክኒኮች ላይ ተግባራዊ ልምምድ ማግኘት መቻላቸዉን አቶ ዳንዔል ገልጸዋል።

በመድረኩ በመገኘት ስለ ስልጠናዉ አጭር ሪፖርት ያቀረቡት የመከላከያ የሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ደረጄ ደመቀ በበኩላቸዉ የመከላከያ የሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ከተቋቋመ ጀምሮ በመከላከያ መሰረተ ልማቶች ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችንና ወንጀሎችን የመከላከል አበረታች ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል።

በዛሬዉ እለት በኢመደአ አማካኝነት የተግባር ስልጠናዎች በሶስት ዙር ያገኙ የሰራዊት አባላት የተሻለ የተግባር ላይ ልምድ በማግኘት አቅም መፈጠሩን አንስተዉ በስልጠናዉ አሁናዊ የሳይበር ምህዳሩ ስጋትና እድሎች ዙሪያ እዉቀት መቅሰማቸዉን ገልጸዋል። በቀጣይም በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር በመስራት የአለማችን ቀዳሚ ስጋት የሆነዉን የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል የሚያስችሉ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።

Publicador de contenidos


የቅርብ ዜናዎች