ኢትዮ-ሰርት በአፍሪካ፣ በመካከለኛዉ ምስራቅና የሙስሊም ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት መካከል በተካሄደ የሳይበር መካላከልና ማጥቃት አቅም አሸናፊ ሆነ
ኢትዮ-ሰርት በአፍሪካ፣ በመካከለኛዉ ምስራቅና የሙስሊም ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት መካከል በተካሄደ የሳይበር መካላከልና ማጥቃት አቅም አሸናፊ ሆነ
በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር #INSA የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል/Ethio-CERRT/ በአፍሪካ መካከለኛዉ ምስራቅና እንዲሁም ከሙስሊም ትብብር ድርጅት አባል ሀገራት በተሳተፉበት የሳይበር መከላከልና ማጥቃት #cyber drill ዉድድር አሸናፊ ሆነ
ለአምስት ቀናት በሞሮኮ ራባት በተከናወነዉ የሳይበር ደህንነት ሳምንትን ላይ ለ13ኛ ጊዜ ለሁለት ቀናት በተከናወነ ዉድድር የተለያዩ ሀገራት የተዉጣጡ የሳይበር መከላከል ላይ የሚሰሩ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን ተቋማቱ ባደረጉት የሳይበር መከላከልና ማጥቃት ዉድድር የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ኢትዮጵያን በመወከል በአንደኝነት አጠናቋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር #INSA በሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል/Ethio-CERRT/ አማካኝነት የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ 24/7 በተጠንቀቅ የሚሰራና የሀገራችንን የሳይበር ምህዳር የሚጠብቅ ተቋም ሲሆን የተገኘዉ ዉጤት ለቀጣይ ስራዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ነዉ።
በሞሮኮ ራባት በተከናወነዉ በዚህ ዉድድር ከ30 በላይ ከሙስሊም ትብብር ድርጅት፣ ከአፍሪካና ከመካከለኛዉ ምስራቅ ሀገራት የተዉጣጡ የሳይበር መከላከል ማዕከላት የተሳተፉ ሲሆን ከኢትዮጵያ በመቀጠል የካዛኪስታን የሳይበር አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ማዕከል፣ የፓኪስታን ብሔራዊ የሳይበር ወንጀል ምርመራ ኤጀንሲ ፣ ኤል ዋይ #LY cert/ እንዲሁም የግብጽ የፋይናንሺያል የሳይበር ክስተት ምላሽ ቡድን #EG-FinCIRT) ከ2ኛ እስከ አምስተኛ ያለዉን ደረጃ ይዘዉ አጠናቀዋል።