ሞባይል ፎን ፍራዉድ / Mobile phone fraud/ ምንድን ነው ?

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ሞባይል ፎን ፍራዉድ ማለት በሞባይላችን ላይ የሚመጡ የማጭበርበር ወንጀሎች ናቸው፤ እነዚህም ዋና መሰረታቸዉ ሞባይሉ ከሲም ጋር ግንኙነት በሚፈጥርበት ጊዜና በኢንተርኔት አማካኝነት በሚመጡ አጭበርባሪዎች የሚከሰት ነው፡፡

ሞባይል ፍራዉድ ከምንላቸዉ መካከል

• ሚስኮል በማድረግ / Missed call scams /

ይህ አይነት የማጭበርበር ወንጀል የይደዉሉልኝ ጥሪ በማስመሰል ደንበኞች መልሰው እንዲደዉሉላቸው በማድረግ ከመጠን በላይ ያላቸዉን ሂሳብ በሰከንድ የመዉሰድ ስልት ነዉ፤

• በጣም ብዙ መልዕክቶችን በመላክ

ይህ ደግም በጣም ብዙ መልዕክቶችን በመላክ የሚመጣ የማጭበርበር ስልት ሲሆን ከመልዕክቶችም መካከል እንደ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፣ ሎተሪ ደርሷችኋል፣ ስኮላርሽፕ እና የመሳሰሉትን መልዕክቶች በመላክ ደንበኞች መልሰው እንዲልኩ፣ እንዲደዉሉ በማድረግ ሚስጥራዊ መረጃን መመንተፍ፣ የባንክ ሂሳብን መዉሰድ እና ሌሎችን ድርጊቶች የመፈጸም ወንጀል ነው፤

• በቀጥታ በመደወል / direct call/

በቀጥታ በመደወል ከትክክለኛ ሰዉ ወይም ከትክክለኛ ድርጅት እንደተደወለ በማስመሰል የተለያዩ መረጃዎችን /ፋይሎችን ወይም ዶክመንቶችን/ መንጠቅ፣ ማንነታችንን የማጣራት፣ የተለያዩ ሚስጥራዊ ኮዶችን፣ አካዉንታችንን፣ የይለፍ ቃላችንን የመመንተፍ እንዲሁም ስኮላር ደርሶሃል ፣ ሎተሪ ደርሶሃል እና የመሳሰሉትን ማታለያዎችን በመጠቀም በዚህ አካዉንት ብር መላክ አለብህ በሚል የሚደረግ የማጭበርበር ስልት ነው፡፡

ከሞባይል ፍራውድ እራሳችንን መከላከል የምንችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?

• የሞባይል አገልግሎት ድርጅቶችን የደህንነት ፖሊሲዎች በደንብ ጠንቅቆ ማወቅና መጠቀም ለምሳሌ PIN ኮድ፣ የይለፍ ቃል፣ ሚስጥራዊ ጥያቄዎችና የመሳሰሉት፤

• ለሞባይሎቻችን ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም፣ በማንጠቀምበት ጊዜ መቆለፍ ፤

• ሚስጥራዊ የሆኑ የግል ወይም የድርጅት መረጃዎችን፡ ለምሳሌ የይለፍ ቃል፣ የአካዉንት ቁጥር፣ኢ-ሜይል አካዉንትና ሌሎችን ዶክመንቶች ከሞባይል ቀፏችን ላይ አለማስቀመጥ፤

• ከማናቃቸዉ የተለያዩ ምንጮች የሚለቀቁ ሶፍትዌሮችንና መተግበሪያዎችን (Apps) አለመጫን፤

• በሞባይላችን የምናያቸዉንና የምንጠቀምባቸዉን ድረ ገጾች URL በጥንቃቄ ማየት ፤

• በማናውቀዉ የሞባይል ቁጥር ለሚደረግ የስልክ ጥሪ ምላሽ አለመስጠት፤

• ሞባይላችን በምንሸጥበት ጊዜ ወይም በስጦታ በምናስተላልፍበት ጊዜ ሁሉንም መረጃዎች ማጥፋታችንንና ወደ ግላችን ሞባይል ማስቀመጣችን ማረጋገጥ መቻል፤

• ማንኛዉንም ዶክመንት ወይም ፋይል በይለፍ ቃል ወይም በኮድ መቆለፍ መቻል፤

• ማንኛዉንም የይለፍ ቃል በየጊዜዉ መቀያየር ተገቢ ነዉ፡፡

Publicador de contenidos