ኢመደአ በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን አስመረቀ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በሰመር ካምፕ መርሃ ግብር በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያሰለጠናቸዉን 237 ባለልዩ ተሰጥዎ ታዳጊ ወጣቶችን በዛሬዉ እለት አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንዔል ጉታ አስተዳደሩ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ከመላው የሀገራችን ክፍሎች በማፈላለግ፣ በመመልመል፣ በማልማት እና በመጠቀም በዘርፉ ብቁና ተወዳዳሪ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ኢመደአ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በየአመቱ የሚያካሂደው “የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ” መርሃ ግብር በዘርፉ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶች በአንድ ማእከል ሆነዉ የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑን አቶ ዳንዔል ጠቁመዋል፡፡

ይህ መርሃ ግብር ከቴክኒካል ስልጠና ባሻገር ታዳጊ ወጣቶቹ በልቡና ውቅር (ማይንድሴት)፣ በስነ-ምግባር እና በአካላዊ ብቃት ብቁ እንዲሆኑ በሚያስችል መልኩ የሚሰጥ ሲሆን፤ ይህም ሰልጣኞቹ ተቋማዊ እና ሀገራዊ ተልእኮን ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ ስብዕና እንዲኖራቸው መሰረት የሚጥሉበት ነው።

የእለቱ የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸዉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተሰጡትን ተቋማዊና ሀገራዊ ተልዕኮዎች በብቃት ለማሳካትና ቀጣይነት ያለውን ሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ደህንነትን ለማረጋገጥ የባለ ልዩ ተሰጥዎ ወጣቶችን ታለንት ወጥ በሆነ መንገድ በመመልመል፣ በማልማት እና በመጠቀም ብቁና በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎች በማልማት ረገድ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ ይበል የሚያስብል መሆኑ ገልጸዋል።

ከዚህ አኳያ በአስተዳደሩ የሳይበር ልሕቀት ማዕከል እየተሰራ ያለውን የታለንት ልማት ሥራ ሀገር አቀፍ መልክና ሽፋን እንዲኖረው ማድረግ ለቀጣይ የሀገራችን የዲጂታላይዜሽን ሽግግር ስኬት መሰረት በመጣል ሂደት ዉስጥ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከኢመደአ ጋር በቀጣይነት እንደሚሰራ ተናግራዋል።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሳይበር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብ/ጄኔራል ደረጀ ደመቀ በበኩላቸዉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከምስረታዉ ጀምሮ ባለ ልዩ ተሰጥዎ ታዳጊዎችን በመመልመል እንደሚሰራ ገልጸዉ ይህን ስራ በተደራጀ መልክ ሰርቶ ተማሪዎችን ለማስመረቅ መብቃቱ የሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ ሂደት ዉስጥ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ጠቁመዋል።

አጠቃላይ ስለ ስልጠናዉ ሂደት የኢመደአ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻዉ በየነ ሪፖርት አቅርበዋል።

Agrégateur de contenus


የቅርብ ዜናዎች