በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ላይ የውይይት መድረክ ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ላይ ከክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

“የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘው 5ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዉስጥ በተለያዩ ሁነቶች በአዲስ አበባ ከተማ ሲከበር የቆየ ሲሆን የወሩ የመጨረሻ መርሃ ግብሮች ጥቅምት 25 እና 26/2017 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የውይይት መድረኮች እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በዚህም በዛሬው እለት በሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊስ ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የመከፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ እንደገለጹት የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት እና ሉዓላዊነት ከምናረጋግጥባቸው ምሰሶዎች መካከል አንዱና ዋነኛው የፖሊሲ ማዕቀፍ ነው፡፡ ይህንንም መነሻ በማድረግ የሀገራችንን አሁናዊና መጻኢ ሁኔታ ለማስተናገድ የሚያስችል ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊስ ወጥቷል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮዎች ፖሊሲው የተፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ በማስተግበርም ሆነ በመተግበር ረገድ የአንበሳውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ ሀገራዊውን የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ ወደመሬት ለማውረድና ለመተግበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን፤ የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ሃኒባል ለማ ለቀረቡት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ አቶ ሃኒባል በማጠቃለያ መልዕክታቸው እንደገለጹት ፖሊሲው የአንድ ተቋም ብቻ አቅጣጫ ጠቋሚ ሳይሆን የሃገራችንን የኢንፎርሜሽ እና የኢንፎርሜሽ መሰረተ-ልማት ደህንነት ማረጋገጫ መሳርያ ነው፡፡ ይህን መሳርያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊጠቀሙበት ይገባል ብለዋል፡፡

アセットパブリッシャー