በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ በማስቀጠል የተጣለበትን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንዳለበት ተገለጸ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“የመሃሉ ዘመን” በእስካሁኑ የለውጥ ሂደት የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት በትጋት መሥራት እንደሚገባ የ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለፁ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች “የመሐሉ ዘመን” በሚል ርእስ በተዘጋጀዉ ወቅታዊ እና ሀገራዊ ሰነድ ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የዉይይት ጽሁፉን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ ያቀረቡ ሲሆን የመሃሉ ዘመን በእስካሁኑ የለውጥ ሂደት የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚሰራበት መሆኑን በማብራሪያቸዉ አንስተዋል።

የሕዝብን ጥያቄዎች በመመለስ፣ አካታች የፖለቲካ ሥርዐት በመዘርጋት፣ የኢኮኖሚ ሪፎርም በማድረግና ዕድገቱን በማስቀጠል፣ የትርክት ለውጥ በማድረግና ፈተናዎችን በመቋቋም በርካታ ስኬቶች በየዘርፉ መመዝገባቸውን አቶ አክሊሉ ገልጸዋል።

ተቋማት እና ግለሰቦች የተጣለባቸዉን ኃላፊነት በብቃት፣ በጥራትና ወቅቱ በሚጠይቀው አግባብ መወጣት ከቻሉ የኢትዮጵያ የብልጽግና ሕልሞች የሚሳኩ ለመሆናቸው ያለፉት ዓመታት ስኬቶች ምስክሮች ናቸው ብለዋል።

“ሀገራችን በለውጥ ሂደት ያለፈችው የለውጡን ቀልባሽ ኃይሎች በመርታት ብቻ አይደለም፤ በርካታ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሠራሽ ፈተናዎችን ጭምር በመሻገር እንጅ” ብለዋል ሚኒስትር ዴኤታው።

በውይይቱ ለተነሱ ሃሳቦች ማብራሪያና ገለጻ ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ሁሉም በየተሰማራበት የተጣለበትን ኃለፊነት በብቃት በመወጣት በለውጥ ሂደቱ የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባዉ አንስተዋል።

እንደ ሀገር የተጀመሩ ሁሉን አቀፍ የለዉጥ ጉዞን በማገዝ እና በማስቀጠል እንደ ተቋም በሀገር አቀፍ ደረጃ ባለፉት ሰባት የለዉጥ ዓመታት በህዝብ የተጣለብንን አደራ በሚገባዉ ልክ ስንወጣ ቆይተናል ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት በእነዚህ አመታት ያገኘናቸው ስኬቶች የሚያዘናጉን ሳይሆን በተሻለ መልኩ ለመፈጸም እንደ መስፈንጠሪያ አድርገን ልንወስደዉ የሚገባ ነው ብለዋል ።

ተቋማችን የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማስጠበቅ በውስጥና በውጭ ያሉ ክፍተቶችንና ተጋላጭነቶችን ነቅሶ በማውጣት በተልዕኮው ስኬት የበኩሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ አኳያ በተቋማችንም ሆነ በሀገራችን የተጀመሩ ማሻሻያዎችን በአግባቡ በመተግበር፣ የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል፣ የተቋማት ግንባታን በማጠናከርና ቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በማገናዘብ በቀጣይ የተጀመረውን ሀገራዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ ሁሉም የተቋሙ አመራርና ሰራተኛ በትጋት መስራትና ይገባዋል ብለዋል።

በቀረበው ወቅታዊ ሀገራዊ ሰነድ ላይ በአስተዳደሩ አመራሮችና ሰራተኞች ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በሰነዱ በቀረቡ መወያያ አጀንዳን መነሻ በማድረግ ለተቋም እድገት መፍጠን ፣ መፍጠር እና መትጋት የግድ የሚልበት ጊዜ ነው ያሉት ዋና ዳይሬከተሯ በስኬቶች ሊደበቁ የሚችሉ ውስጣዊ ክፍተቶችን ያለማቅማማት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተሳፉት የአመደአ አመራር እና አባላት በሰጡት አስተያየት ሰነዱ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰና ተጨባጭ ሁኔታዉን ያገናዘበ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በቀረበው ወቅታዊ ሀገራዊ ሰነድ ላይ በአስተዳደሩ አመራሮችና ሰራተኞች ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኋላ በሰነዱ በቀረቡ መወያያ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

アセットパブリッシャー


የቅርብ ዜናዎች