“የኤርፖርት እና ድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም” የትብብር ስምምነት ተፈረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“የኤርፖርት እና ድንበር አስተዳደር ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም” መተግበር የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጨምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ፣ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት እንዲሁም ጉምሩክ ኮሚሽን የትብብር ስምምነቱን ተፈራርመዋል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት፤ የኤርፖርትና ቦርደር አስተዳደር ስርዓትን በማዘመን ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት መስጠት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ በሆነ መልኩ በማስጠበቅ ብልጽግናችንን ከማረጋገጥ አኳያ ወሳኝ ሚናን ይጫወታል ብለዋል።

ሁላችንም በተናጠል ስንጓዝ አቅማችን የተበተነ ይሆናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ አንዳችን የሁላችንንም የጋራ ጥረት በማቀናጀት የዘርፉን አሁናዊና ቀጣይ ስጋቶች በአግባቡ ምላሽ መስጠት ወቅታዊና አንገብጋቢ ሀገራዊ ጉዳይ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በ9 ተቋማት መካከል በዛሬዉ እለት የተፈረመዉ የትብብር ስምምነት እርስ በእርሷ በከፍተኛ ሁኔታ በተሳሰረችው ዓለም ውስጥ የምናገኛቸውን እድሎች በአግባቡ ለመጠቀም እንዲሁም የሚገጥሙንን ፈተናዎች በብቃት ለመሻገር የሚያስችል ቁመና እንደሚፈጥር በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል።

የተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከትብብር ስምምነቱ በኋላ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት 80ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን አዉደ ርዕይ ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

Contentverzamelaar


የቅርብ ዜናዎች