ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለማረጋገጥ የቁልፍ መሰረተ ልማቶቻችንን የሳይበር ደህንነት መጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የተዘጋጀው 5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት፣ የግል ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት #በሳይንስ_ሙዚዬም ተጀምሯል፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ማሞ ምሕረቱ 5ተኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በይፋ አስጀምረዋል፡፡ በመክፈቻ ንግግራቸውም አለም ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በገባችበት በዚህ ጊዜ “ከሳይበር ደህንነት” ርእሰ ጉዳይ ውጪ ወቅታዊ እና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሌላ አብይ ጉዳይ ሊኖር አይችልም ብለዋል። "የቁልፍ የመሠረተ ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተዘጋጀውን 5ኛውን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን ስናከብር ቁልፍ መሠረተ ልማት የማንኛውም ዘመናዊ ማህበረሰብ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚ እንደመሆኑ መጠን የእነዚህን መሰረተ ልማቶች ደህንነታቸዉን ማረጋገጥ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ሀገራዊ ሉዓላዊነታችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ጉዳይ ነው ሲሉ ክቡር አቶ ማሞ ምሕረቱ ገልጸዋል።

የዲጂታል ሥርዓቱን ነጻና ሉዓላዊነቱ የተረጋገጠ ለማድረግ ለሳይበር ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አቶ ማሞ ምህረቱ በመክፈቻ ንግግራቸው ተናግረዋል፡፡ የዲጂታል ሃብቶችን የመጠበቅ እና የዜጎችን ደህንነት በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ ለሳይበር ደህንነት ትልቅ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ሥርዓት ነጻና ሉዓላዊነቱ የተረጋገጠ እንዲሆንም ለሳይበር ደህንነት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ማሞ ምሕረቱ ለዚህም የባለሙያዎችን አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል በሳይበር ቴክኖሎጂ ልማት የግሉ ዘርፍ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወት በማገዝ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ማበልጸግ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግሥት ሃሚድ በበኩላቸው÷ በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዕቅድ መሠረት የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የሳይበር ደህንነት ወር መከበር የዜጎችን ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር የላቀ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው÷በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን በማክሸፍ ከቢሊየን ብር ኪሣራ መታደግ መቻሉን አስታውሰዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የሳይበር ደህንነት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የሳይበር ወር መከበር ዋና አላማ ሀገራት ለዜጎቻቸው እንዲሁም ለተቋማቶቻቸው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብሮችን ለማከናወን እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

Contentverzamelaar


የቅርብ ዜናዎች