የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እውን እንዲሆን ለሳይበር ደህንነት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እውን እንዲሆን የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ገለጹ።

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው የጂ.አይ.ቴክስ ኤክስፖ (GITEX 2024) እየተካፈሉ የሚገኙት አቶ ዳንኤል ጉታ "የኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እና የሳይበር ደህንነት" በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የፓናል ውይይት ላይ በፓናሊስትነት ኢትዮጵያ የሳይበር ደህንነቷን ለማረጋገጥ እየሰራች ያለችውን ሥራ አብራርተዋል።

ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ስርአት፣ እና የሳይበር ደህንነት እንደሆኑ የጠቀሱት አቶ ዳንኤል፤ ከዚህ አኳያ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን ለማሳካት በአምስት ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሆነ አቶ ዳንኤል አብራርተዋል። እነዚህም: የእዉቀትና ቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ፣ ተቋማዊ ልሕቀት፣ ቁልፍ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥበቃ፣ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ አጋርነትና ትብብር፣ እንዲሁም የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ከማሳለጥ አኳያ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ እና ሌሎች መሰል ተቋማት ትልቅ ሚናን እየተጫወቱ እንደሚገኙ አቶ ዳንኤል በመድረኩ ላይ ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን እና በአጠቃላይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ግቡን እንዲመታ የሚጠበቅበትን ሚና እየተወጣ እንደሆነ አቶ ዳንኤል ጉታ ገልጸዋል።

Contentverzamelaar


የቅርብ ዜናዎች