በፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሚኒስትሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት አመራሮችና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሮች የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን (ኢመደአ) ጎበኙ፡፡

ኢመደአ በሳይበር ደህንነት ላይ እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎች የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ እንደሆነ ሚኒስትሮቹ በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 አንዱ ግብ የሆነውን “በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ፈጠራ የበለጸገ ማሕበረሰብ” የመገንባት ራዕይ ከማሳካት አኳያ በአስተዳደሩ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች ትልቅ ፋይዳ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በራስ አቅም ያለማቸውና ባለቤትነትን ያረጋገጠባቸው የሳይበር ደህንነት ማስጠበቂያ ቴክኖሎጂዎች የሀገሪቱን የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትልቅ እርምጃ መሆኑንም ጎብኚዎቹ ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በሳይበር ታለንት ልማት በኩል ታዳጊ ወጣቶችን በማፍራት ረገድ በአስተዳደሩ እየተሰራ ያለው ሥራ የነገዋን ብሩህና የበለጸገች አፍሪካ አመላካች እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ ፣

የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ " "የወጣቶችን አቅም - ለበለፀገች አፍሪካ - Unlocking the Power of Youth for prosperous Africa” በሚል መሪ ሃሳብ ከመጋቢት 25 እስከ 27/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

Publicador de Conteúdos e Mídias


የቅርብ ዜናዎች