ኢመደአ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ2018 አዲስ ዓመትን በማስመልከት ድጋፍ አደረገ።

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር /ኢመደአ/ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የ2018 አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ 6.6 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ።

በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙትና ድጋፉን ያበረከቱት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሜቄዶንያ የአረጋዊያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በሺዎች ለሚቆጠሩ አረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማን ያልተቆጠበ ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ ትልቅ ልብ የሚጠይቅ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ማዕከሉ ተደራሽነቱን ለማስፋት በሚያደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች ኢመደአ ከሚያደርገዉ የቁሳቁስ ድጋፎች ባሻገር ለማዕከሉ አምባሳደር በመሆን ቀጣይነት ላለዉ የበጎ አድራጎት ስራ የበኩላቸንን እንወጣለን ብለዋል።

የማዕከሉ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ቢኒያም በለጠ በበኩላቸዉ መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እራሳቸውን ችለው መታከም የማይችሉ እና የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ህሙማንን በማንሳት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ያስረዱት ጠቁመዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር/INSA ለማዕከሉ እያደረገ ስለሚገኘው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ወደፊትም የአስተዳደሩ ሰራተኞችን በማስተባበር ድጋፉን እንዲቀጥል ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡