የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ኃላፊነት ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

“የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ቃል በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር #INSA የተዘጋጀው 5ተኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የሀገሪቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት፣ የግል ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት #በሳይንስ_ሙዚዬም ተጀምሯል፡፡

በመክፈቻ ምርሃ ግብሩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሳይበር ደህንነት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ ለ21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ በመከበር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ የሳይበር ወር መከበር ዋና አላማ ሀገራት ለዜጎቻቸው እንዲሁም ለተቋማቶቻቸው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ መርሃ ግብሮችን ለማከናወን እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ዕቅድ መሠረት የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል፡፡  የሳይበር ደህንነት ወር መከበር የዜጎችን ግንዛቤ ከማሳደግ አንጻር የላቀ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘሩ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎችን በማክሸፍ በርካታ ቢሊየን ብር ኪሣራ መታደግ መቻሉን አስታውሰዋል።

ዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሳይበር ደህንነት ከሀገራዊ አጀንዳችን መካከል ግንባር ቀደም መሆን አለበት ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት፤ የሀገራችንን ወሳኝ መሠረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመጠበቅ ጠንካራ የፖሊሲና የሕግ ማዕቀፎችን፣ ደህንነታቸው የተረጋገጠ ቴክኖሎጂዎችን፣ የሰለጠነ የዘርፉ ባለሙያዎችን እና በመንግስትና  እና በግሉ ዘርፍ መካከል ትብብር እና ቅንጅትን መሰረት ያደረገ አካሄዶችን መተግበር ይጠይቃል።

ፖሊሲ ከማዉጣት አንጻር ኢትዮጵያ ወሳኝ እርምጃዎችን ወስዳለች። በተለይም የብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲን በማውጣት። ነገር ግን እነዚህን ፖሊሲዎች በፍጥነት እያደገ ካለው የሳይበር አደጋ ገጽታ ጋር ተጣጣሚና አዳጊ የሆነ የፖሊሲ ትግበራዎችን ካላካሄደች ተፈላጊዉን ለዉጥ ማምጣት አስቸጋሪ ያደርገዋል። ለሀገራዊ ደህንነታችን መረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑትን ስርዓቶች ለመጠበቅ ግልጽ እና አስቻይ የሆኑ ሕጎች፣ ስታንደርዶችን እንዲሁም ሌሎች የማስፈጸሚያ ዘዴዎች አስፈላጊ ናቸው ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናግረዋል

የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ ሌላዉ ቁልፍ ተግባር በቴክኖሎጂ እና በፈጠራ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነዉ። እጅግ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እንደ የምስጠራ ቴክኖሎጂዎችን፣ ዘመኑን የዋጁ የሳይበር ጥቃት የአደጋ ማሳወቂያ ስርዓቶችን በመተግበር እንዲሁም ወቅታዊ የሳይበር ደህንነት መሳሪያዎችን መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከሚሄደው የሳይበር ጥቃት ተቋማችንንና ራሳችንን ለመጠበቅ ወሳኝ ነዉ። የእኛ ወሳኝ የመሠረተ ልማት ስርዓቶች ከመጀመሪያው ጀምሮ የሳይበር ደህንነትን ታሳቢ በማድረግ የተነደፉ መሆን አለባቸው። ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን ታሳቢ ያደረገ አካሄድን /ሴክዩሪቲ ባይ ዲዛይን/ በመከተል ተጋላጭነትን መቀነስ እና የጥቃቶችን ስጋት መቀነስ እንችላለን።

የአቅም ግንባታም ስራ መስራት ሌላዉ ቁልፍ ጉዳይ ነው። የሳይበር ጥቃቶች እያደጉ ሲሄዱ ወሳኝ ስርዓቶቻችንን መከላከል የሚችል የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዳለን ማረጋገጥ አለብን። የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎቻችን ሊከሰቱ ከሚችሉ የሳይበር ጥቃት አደጋዎች ቀድመው መከላከል የሚችሉበትን የስልጠና ፕሮግራሞች፣ የሳይበር ደህንነት ትምህርት እና ቀጣይነት ያለው የአቅም ማጎልበቻ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባቸዋል። ይህ ለአንድ ተቋም አሊያም ለመንግስት ብቻ የሚተው ሃላፊነት አይደለም። የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችና ተቋማትም ጭምር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው።  ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳደሩ ተቋማት የሳይበር ደህንነት ባለሙያዎቻቸውን አቅም ለማጎልበት በጀት መድበዉ መንቀሳቀስ አለባቸው።

የመንግስት እና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ወሳኝ የሆኑ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ደህንነት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የግሉ ሴክተር ከሀገራዊ ደህንነታችን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ፋይናንሺያል እና ኢነርጂ ያሉ በርካታ ስርዓቶችን በባለቤትነት ያስተዳድራል። የሳይበር ስጋቶችን ለመከላከል አንድ ወጥ የሆነ መከላከያ አማራጮችን ለመተግበር በመንግስት እና በኢንዱስትሪ መካከል ያለው ትብብር አስፈላጊ ነው። አንድ ላይ፣ መረጃን መጋራት፣ ውስን የሆነዉን የህዝብ ሃብት በጋራ በመጠቀምና በትብብር በመስራት ሊከሰቱ የሚችሉ የሳይበር ጥቃት አደጋዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት እንችላለን ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ በንግግራቸው ጠቁመዋል።

资产发布器