Asset Publisher

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ያለውን የአቪዬሽን ኤኖቪሽን ኤክስፖን ጎበኙ።

ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት በሚል መሪ ቃል ባሳለፍነው ሰኞ በሳይንስ ሙዚየም በይፋ የተከፈተው የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ግለሰቦች እና ተቋማት በአቪዬሽን ዘርፍ እየሰሩት ያለውን የፈጠራ ስራ ለህዝብ ማስተዋወቅን ውጥን በማድረግ የተከፈተ ነው።

በዚህ የአቪዬሽን ኢኖቬሽን ኤክስፖ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው በዚህ ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙትን የፈጠራ ስራዎች ተመልክተዋል።

በጉብኝቱም ወቅት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፤ ተቋማት እና በግል የፈጠራ ስራቸውን ያቀረቡትን ባለሙያዎችን የጎበኙ ሲሆን በተመለክቱት የፈጠራ ስራዎች መገረማቸውን ገልፀው እኚህን መሰል የፈጠራ ስራዎች ለነገይቱ ኢትዮጲያ ተስፋ መሆን የሚችሉ ናቸው ብለዋል።

ክቡር አቶ ሰለሞን አክለውም ሀገርን ሚያቀኑ ግዙፍ ቴክኖሎጂዎች መነሻቸው እነዚህን መሰል መድረኮች በመሆናቸው የሚመለከታቸው ተቋማት እነዚህን የፈጠራ ውጤቶች እውን አድርጎ ተግባር ላይ ለማዋል በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ፈጠራ ለአቪዬሽን ልህቀት̎ በሚል መሪ ቃል ለህዝብ እይታ በበቃው ኤክስፖ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት በድሮን ቴክኖሎጂ ላይ የሚሰራውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን በአስተዳደሩ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮ ሳይበር ታለንት ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎችም በዘርፉ የሰሯቸውን የፈጠራ ስራዎች ለእይታ አብቅተዋል።

በዚህ ኤክስፖ ላይ ከ90 በላይ ግለሰቦች እና ከ35 በላይ ተቋማት ተሳታፊ ሆነዋል።