የእውቀት ሽግግር መድረኮች ተቋማዊ ተልዕኮን ለማሳካት ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ: ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ: የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሳይበር ደህንነት ዘርፍ ተለዋዋጭ፣ ኢ-ተገማች እና ፈጣን ለውጥ ያለበት በመሆኑ ሁሌም መማር እና የእውቀት ሽግግር ማድረግ በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመዝለቅና ተልዕኮን ለማሳካት ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሯ ይህንን የገለጹት "ስትራቴጂክ ኢንሳይት" የተሰኘ በተቋም ደረጃ በየወሩ የሚካሄድ የውይይት መድረክ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

መድረኩ በዋናነት ኢመደአ በተሰማራበት የሳይበር ኢንዱስትሪ ላይ ያሉ አዝማሚያዎች እና ስትራቴጂክ አሰላለፎች ዙሪያ ለመማማርና ተደማሪ ተቋማዊ ባህል ለመገንባት የሚያስችል ነው።

በመድረኩ የመጀመሪያ የውይይት መድረክ "የባህር እና የየብስ ኮሙኒኬሽን ኬብል ደህንነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አንጻር" በሚል ርዕስ በቀረበ ጥናት ላይ ውይይት ተካሂዷል።

Publicador de contenidos


የቅርብ ዜናዎች