የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢመደአ የክርስትና እምነት ተከታዮች የ2017 ዓ.ም የገና በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሯ በመልዕክታቸዉ የ2017 ዓ.ም የገና በዓልን ስናከብር በሀገራችን በተፈጥሮና በሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችንን በማሰብ፤ ያለንን በማጋራትና ከጎናቸው በመሆን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡

ኢመደአ የሀገራችንን ዲጂታል ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሀገራዊ ፋይዳቸው ላቅ ባሉ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ እየሠራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ወ/ሮ ትዕግስት ይህም ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሳይበር ደህንነት ቁመናን ከፍ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ነገር ግን የዲጂታል ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስራ በአንድ ተቋም ጥረት ብቻ የሚረጋገጥ ባለመሆኑ ሁሉም አካል የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በመልካም ምኞት መልዕክታቸዉ በበዓል ሰሞን የሳይበር ጥቃቶች እንደሚጨምሩ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ ማህበረሰቡ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም የበዓል ሸመታዎች የሚያከናዉንበት፣ ስጦታዎችን በሚገዛበትና የሚለዋወጥበት ወቅት በመሆኑ ለሳይበር ጥቃት አድራሾች የበለጠ ተጋላጭ እንሆናለን ብለዋል።

በመሆኑም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በበዓል ወቅቶች ንቁ ሆነን በመረጃ መንታፊዎች አማካኝነት በሞባይል ባንኪንግ፣ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ሊደርስብን ከሚችል የዲጂታል ማጭበርበሮች እና የማንነት ስርቆት ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የ2017 የገና በዓል ለኢመደአ ማህበረሰብ እና ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን የሰላም ፣የፍቅር ፣ የብልፅግና የመተሳሰብ እንዲሆን በመልካም ምኞት መልዕክታቸዉ አስተላልፈዋል፡፡

Publicador de contenidos


የቅርብ ዜናዎች