የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

Geneste Applicaties

Contentverzamelaar

የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል wo, 20 nov 2024

ቋሚ ኮሚቴው የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት አስተዳደርን የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

ቋሚ ኮሚቴው የኢንፎርሜሽን መረብ ደሕንነት አስተዳደርን የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ vr, 15 nov 2024

ኢመደአ እና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ መስኮች ላይ ዘላቂ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ኢመደአ እና ብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ መስኮች ላይ ዘላቂ ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ vr, 15 nov 2024

የሳይበር ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በኢመደአ እና ፍትሕ ሚንስቴር መካከል ተፈረመ

የሳይበር ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በኢመደአ እና ፍትሕ ሚንስቴር መካከል ተፈረመ vr, 15 nov 2024

Contentverzamelaar

null የተቋማቱን አመራሮች አቅም ለማጎልበት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮች የሥራ አውዳቸውን መሰረት ያደረገ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛል፡፡ ስልጠናው በዋናነት በሥራ ባሕል ግንባታ፣ በዲጂታል ውቅረ ሃሳብ፣ እና በፕሮጀክት አስተዳደር ላይ ያተኮረ ነው፡፡

ስልጠናውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) አስጀምረዋል፡፡

እጅግ ተለዋዋጭ በሆነው የዲጂታል ዓለም ውስጥ ውጤታማ ሆኖ ለመዝለቅ ጠንካራ የሥራ ባሕል መገንባት እና ዲጅታል ውቅረ ሃሳብ ማምጣት እንደሚያስፈልግ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በጋራ ሆነው መውሰዳቸው ከተሰማሩበት የሥራ አውድ አኳያ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጋራ ለመፍታት የሚያስችል መድረክ እንደሆነ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በስልጠና ማስጀመሪያው ላይ ገልጸዋል፡፡

ስልጠናውን እየሰጡ የሚገኙት በጀርመኑ መኪና አምራች መርሰዲስ ቤንዝ ውስጥ ለረዥም አመታት በተለያዩ የሙያና የሃላፊነት ቦታዎች ላይ እየሰሩ የሚገኙት ዶ/ር ጸጋዬ ደግነህ ናቸው፡፡