Asset Publisher

null የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በሞሮኮ እየተዘጋጀ ባለዉ የጂአይቴክስ (GITEX) አፍሪካ ኢትዮጵያን ወክለዉ የተገኙ ስታርታፖችን ጎበኙ

በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ በተካሄደዉ የጂአይቴክስ (GITEX) አፍሪካ ኮንፈረንስ ላይ የአቅም ግንባታ ስራ ለሙያዊ ልህቀትና ኢኮኖሚ ልማት በሚል በተዘጋጀዉ መድረክ ላይ የተካፈሉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ከኮንፍረንሱ ጎን ለጎን ኢትዮጵያን ወክለዉ የተገኙ ስታርታፖችን ጎብኝተዋል።

በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደዉ እና ትኩረቱን በሳይበር ደህንነት፣ በክላዉድ ኮምፒዉቲንግ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በፊንቴክ (fintech)፣ በዲጂታል ከተማ፣ አግሪ ቴክ (agritech) እና መሰል የቴክኖሎጂ ዘርፎች ባደረገዉ ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያ በመድረኩ ምርትና አገልግሎቶቿን እያስተዋወቀች ትገኛለች።

በጉብኝቱ ወቅት በሳይበርና መሰል ጉዳዮች ላይ አቅም ያላቸዉ አካላት ከኢመደአ ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባና ተቋሙ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።

በጉብኝቱ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተሳትፈዋል።