ተቋማት ራሳቸዉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የሚያደርጉት ጥረት “ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስኬት መሰረት የሚጠል ነዉ፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
Asset Publisher
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለምቶ በዛሬዉ ዕለት በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመረቀዉ ‘ስማርት የኮርት’ ሲስተም እንዲሁም በቀጣይ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና በኢትዮ-ቴሌኮም የሚተገበሩ የቴክኖሎጂዎች የሃገራችንን የዳኝነት ሥርዓት እንደሚያዘምኑ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ተናገሩ።
ይህም እንደ ሃገር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እዉን እንዲሆን የምናደርጋቸዉን ጥረቶች የሚደግፉና የዲጂታል ሽግግሩን የሚያፋጠኑ መሆናቸዉን ዋና ዳይሬክተሩ በመድረኩ ተናግረዋል።
የአርተፍሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ‘የስማርት የኮርት’ ስርዓት አልምቶ በማስመረቁ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ዋና ዳይሬክተሩ በቀጣይም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና ኢትዮ-ቴሌኮም የጠቅላይ ፍርድ ቤትን ስራ የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂዎችን እንደሚተገብሩ ጠቁመዋል።
እንደ ተቋም ኢመደአ ከፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በሚገባዉ ዉል መሰረትም የጠቅላይ የፍርድ ቤቱን አሰራር የሚያልቁ ደህንነታቸዉ የተጠበቀ የኮሚዩኒኬሽን ስርዓት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ ስርዓት እንዲሁም የዳኝነት አገልግሎቱን በከፍተኛ ደረጃ አዉቶሜት (Automate) እንደሚያደርግ ክቡር አቶ ሰለሞን ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገር የፍርድቤቱን አገልግሎት የሚያቀላጥፉ የተቀናጀ የጉዳዮች አስተዳደር መረጃ ስርዓት እና ኤሌክትሮኒክ መዛግብት አስተዳደር ስርዓት እንደሚተገበሩ ጠቁመዋል።