የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አመራርና ሰራተኞች የችግኝ ተከላ እና የቤት እድሳት መርሃ ግብር አካሄዱ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) አመራርና ሰራተኞች “የሚተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ/የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እና የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የተጀመረው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡

ኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት /ሮ ትግስት ሃሚድ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያን አረንጓዴ ምድር ለማድረግ የተጀመረው #አረንጓዴዓሻራ ኢኒሼቲቭ በሐገራችን ተፈጥሯዊ ሥነ ምህዳር ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው ብለዋል፡፡ ባለፉት 5 የአረንጓዴ ዓሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እንደ ሀገር ከ25 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ተክለናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርም በዚህ ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ በንቃት በመሳተፍ እንደ ተቋም በየአመቱ የአረንጓዴ ዓሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮችን ከማካሄድ ባሻገር፤ የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ በኩልም አርአያ ሊሆን የሚችል ሥራ ሰርተናል ብለዋል፡፡ በሌላም በኩል በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር እና የጽድቀት መጠን ለመከታተል የሚያስችል ሲስተም በማበልጸግ አረንጓዴ ዓሻራ ኢኒሼቲቭ ስኬት የጎላ አስተዋጽኦ አበርክተናል ሲሉ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ እንደ ተቋም የሀገራችንን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ኢትዮጵያን አረንጓዴና ጽዱ  በማድረግ ሂደት ተቋማዊ አሻራችንን እንወጣለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዛሬው እለት ከተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ጎን ለጎን የክረምት የበጎ ፈቃድ የቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብርም ተከናውኗል፡፡