ኢመደአ የደራሽ የተቀናጀ የክፍያ ስርአትን ቀጣይ አጠቃቀም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ለምቶ ከስድስት አመታት በፊት ወደ አገልግሎት የገባዉ ደራሽ የተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም ቀጣይ አጠቃቀም ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።

ኢመደአ በክፍያ ፕላትፎርሙ ላይ በትብብር እየሰሩ ካሉ 21 ባለድርሻ አከላት ጋር ምክክር ያደረገ ሲሆን በዚህ ምክክር የተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች፣ የፋይናንስና እና ሌሎች የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተገኝተዋል።

የዉይይቱ ትኩረትም ፕላትፎርሙ ባለፉት ስድስት ዓመታት የአገልግሎት ክፍያ ሳያስከፍል መቆየቱን እና በቀጣይ ግን የደራሽ ፕላትፎርምን ኦፕሬሽናል ወጪዎቹን ለመሸፈን እንዲሁም ስርዓቱን ለማዘመን ተመጣጣኝ ክፍያ ማስከፈል የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነበር።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ የሀገራችን የዲጂታል ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ልትሰራው ከሚገባት ስራዎች አንዱና ዋንኛው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ደራሽ የተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም ከስድስት አመታት በፊት ልክ እንዳሁኑ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በስፋት ባልነበሩበት ወቅት የለማ እና ተቋማችን የሀገራችንን የቴክኖሎጂ ባላቤትንነት ለማረጋገጥ እያደረገች ያለችዉን ጥረት ማሳያ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በመድረኩ መክፈቻ ፕላትፎርሙ አሁን ከሚሰጠው ግልጋሎት በተሻለ ደረጃዉን ከፍ ለማድረግ እና ሀገራችን ለዲጂታል 2025 ልታሳካው ያለመችውን ውጥን ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲተባበሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የነበረዉን የውይይት የመሩት የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ በበኩላቸዉ ደራሽ ፕላትፎርም መንግስት የተለያዩ የዲጂታል የክፍያ ስርዓቶችን በመጠቀም የሚፈጸሙ የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመፈተሸ እና አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአገልግሎት ክፍያ ስርዓት መሆኑን ተናገረዋል።

በዚህ ዉይይት መድረክም ፕላትፎርሙን አስመልክቶ እስከ ዛሬ ባጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎች እንዲሁም በደራሽ በሚፈጸሙ የአገልግሎት ከፍያ አግባቦች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

ደራሽ የተቀናጀ የክፍያ ፕላትፎርም በአሁኑ ሰዐት 21 ከሚሆን የግልና የመንግስት ባንኮች ጋር በመቀናጀት የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ያስቻለ ሲሆን በዚህም ከገቢዎች ሚኒስቴር በተፈጠረ ቅንጅት በደራሽ ፕላትፎርም 90 ቢሊየን ብር በዓመት መሰብሰብ ተችሏል።