የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ #ETEX2025 ኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሰጠችውን ትኩረትና ቁርጠኝነት ለማሳየት የሚያስችል መድረክ ነው

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (Ethiopian Technology Expo - ETEX2025) ኢትዮጵያ ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሰጠችውን ትኩረትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ኤክስፖ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ፡፡

ክብርት ዋና ዳይሬክተሯ በኤክስፖው የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንደገለጹት የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ኤክስፖ #ETEX2025 ኢትዮጵያ በሳይበር ደህንነት፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በስማርት ከተማ፣ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በቴክኖሎጂ ትምህርት በአጠቃላይም በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ የመጣንበትን ርቀትና ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች፤ በቀጣይ ልንደርስበት የምንፈልገውን ራዕይ ለማሳየት የሚያስችል መድረክ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን ሀገራችንን ወደ ብልጽግና የምናሻግርበት ቁልፍ መሳሪያ ነው ያሉ ዋና ዳይሬክተሯ፤ ለዚህም በትምህርት፣ በጤና፣ በጸጥታና ደህንነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ ወ.ዘ.ተ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም እየተሰራ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት እና ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ አኳያ በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከእነዚህም ስኬቶች መካከል ቁልፍ የሕዝብ መሰረተ ልማት (Public Key Infrastructure - PKI) የዳታ ማዕከል መገንባት መቻሉ፤ ደህንንነታቸው የተረጋገጠ የግንኙነት ፕላትፎርሞችን በማልማት የቴክኖሎጂ ባለቤትነትን ማረጋገጥ መቻሉ፤ የሳይበር ወንጀሎችን ለመመርመር የሚያስችል ዘመናዊ የዲጂታል ፎረንሲክ ላብራቶሪ መገንባቱ፤ በአጠቃላይ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ቁልፍ የዲጂታል መሰረተ ልማቶች መገንባታቸውን ዋና ዳይሬክተሯ አንስተዋልl::

በሌላም በኩል በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምርምርና ልማት ዙሪያ በርካታ ቁልፍ ሥራዎች መሰራታቸውንም ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡ ዲጂታል መታወቂያ፣ የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ የሥልጠና ኢኒሼቲቭ፣ የመንግሥት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራዎች፣ የስማርት ከተማ ልማት ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ በስኬት የሚታዩ ዘርፎች መሆናቸውን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡