የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የብሄራዊ ደህንነትን እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው
የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የብሄራዊ ደህንነትን እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው
የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ የብሄራዊ ደህንነትን እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሆነ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሳይበር ደህንነት ካውንስል ሊቀመንበር መሃመድ አልኩዌቲ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ 3ETEX2025 የመክፈቻ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት ዶ/ር መሃመድ እንዳሉት ሀገራት ጠንካራና የማይበገር የሳይበር ደህንነት አቅም ለመገንባት በትብብር መስራት ይገባቸል ብለዋል፡፡
ከዚህ አኳያ የአፍሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በሳይበር ደህንነት መስክ በጋራ ተቀናጅተው በመስራት ቀጠናዊ የሳይበር ደህንነት አቅምን ማጠናከር እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
(ዶ/ር) መሃመድ አልኩዌቲ በኤክስፖው መክፈቻ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ የተሰሩ ሥራዎችንና መልካም ተሞክሮዎችን በመድረኩ ላይ አጋርተዋል፡፡
በዚህም በሰው ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የመጪውን ጊዜ ውስብስብ የሳይበር ጥቃት አስቀድሞ ለመከላከል ወሳን መሆኑን ገልጸዋል፡፡