በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ኢትዮጵያ በ1888 በአድዋ ጦርነት በወራሪዎች ላይ የተቀዳጀችዉ ድል የአፍሪካ ቀጣይ የታሪክ ጅረት ዉስጥ ወሳኝ ሚና መዉጣቱን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ።

በአድዋ ጦርነት የታየዉ ተምሳሌታዊ ተግባር የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ሊደገም እንደሚገባ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ ጠቁመዋል።

ድሉ ቀኝ ገዢዎችን አንገት ያስደፋ ኢትዮጵያን ነፃነት ያጎናፀፈና ለጥቁር ህዝብ የይቻላል መንፈስ የፈጠረ ትልቅ የታሪክ ክስተት ነው ብለዋል።

ዛሬ ጦርነቱ ስፍራዉን ቀይሯል ያሉት ወ/ሮ ትዕግስት ጦርነቱ ድንበር ወደሌለዉ፣ ዉስብስብና ኢ-ተገማች ወደሆነዉ ሳይበር ጦርነት መምጣቱን ገልጸዋል።

የኛ ትዉልድ የነጻነት ተጋድሎ ሀገራችን በምታደርገዉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በመደገፍና ይህን ተከትሎ የሚከሰቱ የሳይበር ጥቃቶችን በመመከት እና የሳይበር ጦርነቶችን በበላይነት በመወጣት የሚገለጽ መሆኑን አንስተዋል።

የዛሬ 129 ዓመት ኢትዮጵያውያን አርበኞች በአድዋ ጦርነት ባደረጉት ተጋድሎ መሬታቸውን ከወራሪዎች እንደተከላከሉ ሁሉ ኢመደአም ጠንካራ የሳይበር መከላከል አቅም በመፍጠር፣ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን በማበረታታትና ከዉጪ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በመቀነስ የራሱን ሚና እየተወጣ ነዉ ብለዋል።

ከዉጭ በሚገቡ የቴክኖሎጂ ምርቶችና ፕላትፎርሞች ላይ ጥገኛ በመሆን የብሄራዊ ደህንነትንና ብሄራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ፤ የዲጂታል ሉዓላዊነት ማረጋገጥ እንደማይቻል ወ/ሮ ትዕግስት ገልጸዋል።

የዲጂታል ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅም ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ማበልጸግና መጠቀም፣ የሳይበር ደህንነት እውቀቶችን ማሳደግ፣ ብቁ የሰዉ ሀይል ማልማትና የማህበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊና ማሳደግ ወሳኝ ነዉ ብለዋል።

የአድዋ ድል ለአሁኑ ትዉልድ ካስተማረን ትምህርቶች ዉስጥ ነፃነት የሚገኘው በስትራቴጂያዊ እሳቤ፣ በጽናት እና በራስ በመተማመን መሆኑን አሳይቶናል ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የአድዋ መንፈስ ወደ ሳይበር ምህዳር በማምጣት የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ በኢትዮጵያውያን እጅ እንዲቆይ ማድረግ እንደሚገባ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ ገልጸዋል።

“አድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል”

资产发布器


የቅርብ ዜናዎች