ኢመደአ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አቅም ያላቸዉን ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን  ከፍተኛ የስራ አቅም ያላቸው ኮምፒውተሮች ድጋፍ አደረገ፡፡

በድጋፍ አሰጣጥ መርሐ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪና የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለሚዲያዎች ድጋፍ ሲያደርግ የመጀመሪያው እንዳልሆነ አንስተዋል።

ዘመኑ የዲጂታል በመሆኑ ፋናን ለማዘመን እና ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር እንዲጓዝ የተሰጠው ድጋፍ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡ የዛሬዉ ድጋፍ ከትላንቱ የቀጠለ ለነገዉ መነሻ የሆነ መሆኑን ያወሱት ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሀገራችን ያሰበችዉን ብልጽግና ለማምጣትም ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑን በድጋፍ መርሃግብሩ ላይ ተናግረዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በትብብር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ ኢመደአ ያደረገው ድጋፍ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዲጂታል ሚዲያ ዘርፉን እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማዘመን እንደሚያግዝ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽንን ከሳይበር ጥቃት የመከላከል ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዉ፣ ለሰራተኞች  የሳይበር ደህንነት የንቃተ ህሊና (cyber security Awareness) ስልጠና በመስጠትና መሰል ጉዳዮች ላይ በቀጣይም ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በተለያዩ ዘርፎች በጋራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድማሱ ዳምጠው፣ ለፋና ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፤ የተቋማቱ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ዛሬ የአስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች በፋና ዋናው መስሪያ ቤት በመገኘት ያደረጉት ድጋፍ የሁለቱን ተቋማት መልካም ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ ነው።

资产发布器


የቅርብ ዜናዎች