የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ በፍጥነት ጸድቆ ተግባር ላይ መዋል እንደሚገባ ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የቁልፍ መሰረተ ልማቶችን የሳይበር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የህግ ማዕቀፍ በፍጥነት ጸድቆ ተግባር ላይ መዋል እንደሚገባ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው "የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የጥናት ሰነድ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቀረበበት ወቅት ነው። ከጥናት ሰነዱም በተጨማሪ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሪፎርም ጉዞ ላይ ለምክር ቤት አባላቱ ገለጻ ተደርጓል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማስከበር ረገድ የሀገሪቱ መከታና ኩራት መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልፀዋል።

ኢመደአ እየሰራቸው የሚገኙ የተለያዩ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች የሀገርን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ከማረጋገጥ ባሻገር ተቋሙን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪ እንደሚያደርገው የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተቋሙ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተለያዩ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን፣ በዚህም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውንና በቀጣይም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በሌላም በኩል "የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት በኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ ተዘጋጅቶ በቀረበው የጥናት ሰነድ ላይ ቁልፍ መሰረተ ልማቶች ለሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊና ፖለቲካዊ እድገት ላይ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተመላክቷል።

እንደ ሀገር በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ከምንጊዜውም በላይ እየጨመሩ መምጣታቸውን በጥናቱ ላይ ተገልጿል። በተለይም በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ ጉዳት ቢደርስባቸው በሀገር ጥቅምና ደህንነት እንዲሁም በዜጎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ የሚፈጥሩ በመሆናቸው ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተገልጿል።

ከዚህ አኳያ የሀገሪቱን ቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት የማስጠበቅ ሃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር "የቁልፍ መሰረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት" ረቂቅ አዋጅ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ይህንኑ አዋጅ በፍጥነት አጽድቆ ተግባር ላይ ማዋል አጠቃላይ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ተገልጿል።

Publicador de continguts


የቅርብ ዜናዎች