በኢመደአ እና በማዕድን ሚንስቴር መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) እና የማዕድን ሚንስቴር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ፤ በአቅም ግንባት፣ የእውቀት መጋራት እና የዲጂታል መሰረተ ልማትን ለመጠበቅ እንዲሁም የተሳለጠ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለመዘርጋት በአጋርነትና በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እና የማዕድን ሚንስቴር ሚኒስትር ክቡር ኢንጅነር ኃብታሙ ተገኝ ፈርመዋል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ልማት አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ዋና ዋና ዘርፎች መካከል አንዱ መሆኑን የገለጹት የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፤ ከዚህ አኳያ ሀገሪቱ ከዘርፉ ለማግኘት ያቀደችውን ገቢ ለማሳደግ እና ዘመናዊ የማዕድን ልማት ለመገንባት የዘርፉን አሰራር ዲጂታላይዝ ማድረግ እንዲሁም የሳይበር ደህንነቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከማዕድን ሚንስቴር ጋር የተደረገው የመግባቢያ ስምምነትም በሁለቱ ተቋማት መካከል ቀድመው የተጀመሩ የትብብር ሥራዎችን ይበልጥ በማጠናከር አጠቃላይ የሀገሪቱን የማዕድን ሃብት በላቀ ደረጃ ለመጠቀም የሚያስችል እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

የማዕድን ሚንስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር ኃብታሙ ተገኝ በፊርማ መርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ዲጂታላይዜሽን የዘመኑ ዋና የልሕቀት መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን የማዕድን ኃብት በማልማት አገሪቱ በዘርፉ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ ዘርፉን ማዘመንና ዲጂታላይዝ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ጋር የተደረገው ስምምነት በዓለማቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የማዕድን ኢንዱስትሪ ለመገንባት አስቻይ ሚናን የሚጫወት እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ኢመደአ የኢትዮጵያን የሳይበር ደህንነት ከማረጋገጥ ባሻገር የተቋማትን የአሰራር ስርአት ለማዘመን የሚያስችሉ ምርትና አገልግሎቶችን በማልማትና በማስታጠቀ ረገድ ከፍተኛ ሚናን እየተጫወት ይገኛል ያሉት ኢንጅነር ኃብታሙ ተገኝ፤ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው ስምምነት የማዕድን ሚንስቴር እና በስሩ የሚገኙ ተጠሪ ተቋማትን የአሰራር ስርአት ለማዘመን እና የላቀ የአሰራር ስርአት ለመዘርጋት ጉልህ ሚናን የሚጫወት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት መሰረት ያደረገ የኮንትራት ስምምነት የተፈረመ ሲሆን፤ ስምምነቱን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ እና የኢመደአ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃኒባል ለማ ፈርመዋል፡፡

Publicador de continguts


የቅርብ ዜናዎች