የአንካራዉ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለዉን ጥረት አንድ ርምጃ ከፍ ያደረገ መሆኑን የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለጹ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

በአንካራ የተፈረመዉ የኢትዮ-ሶማሊያ ስምምነት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን እያደረገች ያለዉን ጉዞ አንድ ርምጃ ከፍ ያደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ተናገሩ።

ይህን ያሉት በዛሬዉ እለትም በአንካራው የኢትዮ-ሶማሊያ የባህር በር ስምምነት ላይ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር መካከለኛና ከፍተኛ አመራሮች ዉይይት ባደረጉበት ወቅት ነዉ።

በውይይቱ ላይ “የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ እና የአንካራው ስምምነት አንድምታ ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር” በሚል ርእስ የኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ የመነሻ ጽሑፍ አቅርበዋል።

በጽሑፉ ብሄራዊ ጥቅም ሀገራት እንደ ሀገር እንዲቆሙ ከሚያደርጓቸው ቁልፍ ምሰሶዎች እና መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው መሆኑ እና የባህር በር ጉዳይ ደግሞ አንደኛው የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ በመሆኑ የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ጉዳይ ከታሪክ፣ ከሕግና ከሕዝብ አሰፋፈር አኳያ ተገቢነቱና አስፈላጊነቱ ላይ ዉይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩትና የማጠቃለያ ሃሳብ የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ባስተላለፉት መልዕክት ጉዳዩ ለሀገር ብሔራዊ ጥቅም እና ደህንነት ካለው ከፍተኛ ፋይዳ አኳያ እና ኢመደአም የብሔራዊ ደህንነትን የማስጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ተቋም ውይይቱ ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በመሆኑም “ሀገራችን ኢትዮጵያ ከባለፉት ጊዜያት የመሽኮርመም አካሄድ ወጥታ በክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ መሪነት የባህር በር ጉዳይን በድፍረትና በግልጽ በአጀንዳነት አንስታ ጥበብ በተሞላበት አመራር እዚህ ደረጃ ላይ ማድረስ በመቻሏ ትልቅ ድል ነው” ብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ከሰሞኑ በተርኪዬ አደራዳሪነት በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል በአንካራ የተደረገው የባህር በር ስምምነት ትልቅ አንድምታ ያለውና ጉዳዩን አንድ እርምጃ ወደፊት ያራመደ ትልቅ ስኬት መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ኢመደአ እንደ ተቋም ጉዳዩን በሚመለከት ከውስጥም ከውጭም የሚነዙ አፍራሽ የሀሰት መረጃዎችን በማጋለጥና ከፊት ሆኖ እውነታውን ለሕዝብ በማድረስ የተጀመረውን የባህር በር የማግኘት ጉዞ ከግብ ለማድረስ ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።

Publicador de continguts