የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የ2017 ዓ.ም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሃሚድ ለኢመደአ ሰራተኞች እና ለመላዉ ኢትዮጵያዊያን 2017 አዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላላፉ።

2017 . አዲስ አመት ብሩህ ዘመን እንዲሆን መልካም ምኞታቸዉን የገለጹት / ትዕግስት ክፋትን የምናስወግድበት መተጋገዝና ትብብር የሚሰፍንበት፣ ጥላቻን የምናርቅበትና አንዳችን ለሌላችን መከታ ከለላ የምንሆንበት እጅ ተያይዘን ወደፊት የምንሻገርበት አዲስ አመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት እንደሚያስጠብቅ ተቋም ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ በዲጂታል ምህዳር ላይ ያለምንም ስጋት ግብይት የሚፈጽምበት እንዲሁም መረጃ በነጻነት እንዲለዋወጥ ለማድረግ 24 ሰአት 7ቱንም ቀናት እየሰራ ነዉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ የሚቻለዉ ሁሉም ተቋማት እና ዜጎች የየራሳቸውን የሳይበር ደህንነት በማስጠበቅ ሚናቸውን መወጣት ሲችሉ ነው ብለዋል፡፡  

የበዓላት ግርግር ለሌባ ምቹ እንደሆነው ሁሉ በዲጂታል ምህዳሩም የሳይበር ወንጀለኞች በበአላት ወቅት የሚካሄደውን ከፍተኛ የሆነ የዲጂታል የባንክ አገልግሎትና ግብይት እንዲሁም የመረጃ ልውውጥ መነሻ በማድረግ የተለያዩ አይነት የሳይበር ወንጀሎችን ለመፈጸም የሚነሱበት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ከዚህ አኳያ ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል በበአላት ወቅት ከሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እራሱን መጠበቅ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

መጪው 2017 አዲስ አመት ለመላ ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የፍቅርና፣ የመተሳሰብ እንዲሆንም ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Asset Publisher