በተባበረ መንፈስ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እዉን ማድረግ ይገባል፡ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ውጥኖችን የተመለከተ ኤግዚቢሽን አና አውደ ጥናት በዛሬዉ እለት በሳይንስ ሙዚየም የኢፌዲሪ ም/ጠ/ሚንስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ሚንስትሮችና ሌሎች የተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ተካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ “የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞና ዉጥኖች” ዙሪያ ገለጻ ያቀረቡ ሲሆን በገለጻቸዉም በተባበረ መንፈስ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እዉን ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽ ጉዞ በዋናነት ሀገራዊ ፍላጎቶችን የሚመልስ፣ ወጪ ቆጣቢና ደህንነቱ የተጠበቀ በሆነ መልኩ እየተተገበረ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ከየት ተነሳን፤ አሁን ምን ላይ እንገኛለን፤ በቀጣይ ምን አቅደናል፤ በሚለዉ ላይ ሰፊ ገለጻ ያቀረቡት ወ/ሮ ትዕግስት በተለይም የብሄራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አባል የሆኑ ተቋማት (ኢመደአን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት) በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስተባባሪነት በርካታ አቅሞችን መገንባት መቻላቸዉን ጠቁመዋል።

ተቋማቱ በመሰረተ ልማት ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማት፣ በሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ እንዲሁም የህግ ማዕቀፎች ላይ ሰፊ ስራዎች መሰረታቸዉን ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት በወሳኝነት የሰዉ ሃይል ልማት ላይ መስራት እንደሚገባ የገለጹት ወ/ሮ ትዕግስት ከዚህ አኳያ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ይፋ የሆነዉ የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ማሳያ መሆኑን ወ/ሮ ትዕግስት ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካዉንስል አባል ተቋማት የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን በሳይንስ ሙዚየም በዛሬዉ ዕለት የተከፈተ ሲሆን ኤግዚቢሽኑ ለአንድ ሳምንት ይቆያል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች