የከተማ አስተዳደሩ የዲጂታል ካዳስተር ሥርዓት ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገለጸ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የዲጂታል ካዳስተር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍና የኤሌክትሮኒክስ የመሬት አገልግሎት ስርዓት በይፋ ተመርቋል፡፡

የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የዲጂታል ካዳስተር ፕሮጀክትና የኤሌክትሮኒክስ የመሬት አገልግሎት ስርዓት በአደማ ከተማ አስተዳደርና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ትብብር ለምቶ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ትዕግስት ሃሚድ፤ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም የዲጂታል ካዳስተርና የኤሌክትሮኒክስ የመሬት አገልግሎት ስርዓቱ ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎችን ለመፍታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

የአዳማ ከተማ እንደ ሀገር የዲጂታል የመሬት አጠቃቀም ካዳስተር ሥርዓትን ለመተግበር ከተመረጡ አምስት ከተሞች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ሥርዓቱን ለመተግበር የከተማ አስተዳደሩ ባሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ዲጂታል ካዳስተር ሥርዓትን በመዘርጋት የመጀመሪያ ሊሆን መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ከተሞች ክላስተር አስተባባሪ አቶ መስፍን መላኩ በበኩላቸው፤ በኦሮሚያ ክልል የመሬት አገልግሎት አሰጣጥን ዲጂታላይዝ በማድረግ በዘርፉ የሚታየውን ህገ ወጥነት ለመቆጣጠር ትኩረት መደረጉን በምረቃ ስነስርዓቱ ተናግረዋል፡፡

በዚህም የክልሉን ከተሞች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የመሬት ዘርፉን አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታል በማድረግ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም በአጠቃላይ ከከተሞች መሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚታየውን ሌብነትና ዝርፊያ እንዲሁም ህገ ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከል ሚናው የጎላ መሆኑን ሃላፊዉ ጠቁመዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው፣ የካዳስተር ስርዓት እውን ለማድረግ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ሙከራዎች ቢደረጉም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት መገባቱን አንስተዋል። የአዳማ ከተማም ለሁሉም የኢትዮጵያ ከተሞች ምሳሌ በሚሆን መልኩ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ፣ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓትን እውን ማድረጉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው፤ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተሰሩ የተጠናከሩ ሥራዎች የከተማዋን የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉንና ይህም የከተማዋን መሬት በአግባቡ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማቶች እንዲውል የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች