የስማርት ከተማን ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ይገባል - ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የስማርት ከተማን ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገለፁ።

ዋና ዳይሬክተሯ ይህንን የገለጹት የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ “የሳይበር ደህንነት ለስማርት ሲቲ” በሚል መሪ ሃሳብ ባዘጋጀዉ ሲምፖዚየም ላይ ነው።

አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን በሚመጥን መልኩ እየተለወጠች ትገኛለች ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ከተማዋ ወደስማርት ሲቲ በምታደርገው ጉዞ ለሳይበር ጥቃት ተጋላጭ እንዳትሆን የሳይበር ደህንነት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። የስማርት ከተማን ለመገንባት የሚከናወኑ የቴክኖሎጂና የአሰራር ስርዓት ስራዎች የሳይበር ደህንነትን ማዕከል ያደረጉ መሆን አለባቸው ብለዋል። ለዚህም የዜጎችን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማሳደግና የሳይበር ስጋት መረጃ መለዋወጥ ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን አማረ በበኩላቸው እንደገለጹት አዲስ አበባን ስማርት ለማድረግ የሚያስችል እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው ስማርት ሲቲ አገልግሎትን ከማዘመን ጋር ተያይዞ ጊዜውን የዋጀ የሳይበር ደኅንነት አቅምን የመገንባት ጉዳይ ከወዲሁ ሊሰራበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ከዚህ አኳያ ቢሮው የስማርት ሲቲ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደስራ መግባቱን ተናግረዋል። የሳይበር ደህንነት በስማርት ሲቲ የሚሰሩ የዲጂታል መሰረተ ልማትና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠበቅ እንደሚረዳም አቶ ሰለሞን አማረ ተናግረዋል።

"የሳይበር ደህንነት ለስማርት ከተማ" በሚል መሪ ሀሳብ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች