የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲን ጎበኙ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ሃሚድ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በከተማው የተቋም ግንባታ በዋናነትም የዲጂታላይዜሽን ስራ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በዋና መ/ ቤት ተገኝተው ጎብኝተዋል።

የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር / ትዕግስት ኤጀንሲው እያደረገ ያለውን የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የዲጂታላይዜሽን ስራ የተመራበትን መንገድ ያደነቁ ሲሆን በሃገራዊ የዲጂታል ሃገር ግንባታ ላይ ተቀራርቦ በመስራት ውጤት ማምጣት እንደሚገባም  ገልፀዋል።

/ ትዕግስት ከተማው ለሴክተሩ የሰጠው  ትኩረት የሚበረታታና ለሌሎች አርዕያ እንደሆነ ያነሱ ሲሆን፤ ኢመደአ በሳይበር ደህንነትና መሰል ጉዳዮች ላይ ስልጠና፣ ቴክኖሎጂ ምርቶች ፍተሻና ግምገማ የቴክኖሎጂ ዘርፉን በማጠናከር በተለይም የሳይበር ደህንነት የስራ ክፍልን በማቋቋም ሂደት እና መስል ጉዳዮች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸዉ የተቋማቸዉን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እየሰራ ያለውን ስራ ያብራሩ ሲሆን ዋና መ/ ቤት ላይ የተሰሩ ስራዎች እና ተቋሙ በቀጣይ ግብ አስቀምጦ በትኩረት እየሰራ  መሆኑን ጠቁመዋል።

ከትኩረት መስኮች መካከልም በዋናነትም ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ጥራትና ተደራሽነት  ጋር ያሉ እቅዶች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።