የኢመደአ የ2017 ዓ.ም የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ምዝገባ ተጀመረ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) #INSA ላለፉት ሦስት ተከታታይ አመታት በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸዉን ታዳጊዎች እየመለመለ በማሰልጠን ወደ ተቋሙ እና ወደ ሳይበር ኢንዱስትሪዉ እንዲቀላቀሉ ሲያደርግ ቆይቷል።

በያዝነው 2017 ዓ.ም ከባለፉት ሦስት አመታት በተሻለ ሁኔታ በመላ ሀገሪቱ ልዩ ታለንት ያላቸዉን ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት እስከ ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ያሉ በመመልመል ለ4ኛ ዙር ለማሰልጠን ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም በሳይበር ደህንነት፤ በዴቨሎፕመንት፤ በኢምቤድድ ሲስተም እና በኤሮስፔስ ላይ ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት (Talent with passion) ያላችሁ በታለንት ማእከሉ የቴሌግራም ቻናል ( https://t.me/cteinsa ) በመግባት ስለ ፕሮግራሙ በቂ መረጃ ማግኘት የምትችሉ ሲሆን ቻሌንጁን ለመመዝገብ የሚከተለዉን ሊንክ ተጠቅማችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። https://talent.insa.gov.et

Asset Publisher