የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ቀድሞ በመለየት፣ በማክሸፍና በመቆጣጠር የሃገራችን የሳይበር አቅም ማሳያ ተቋም ነው - ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን፡ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ቀድሞ በመለየት፣ በማክሸፍና በመቆጣጠር የሃገራችን የሳይበር አቅም ማሳያና የሃገር ኩራት የሆነ ተቋም እንደሆን የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን በ4ኛው ሃገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ፕሮግራም እና በኢመደአ በቀረበው “ሥውር ውጊያ” የፊልም ምርቃት መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የሳይበር ምህዳር እንደ ኢትዮጰያ በቴክኖሎጂው ብዙም ባላደጉ ነገር ግን በጂኦ-ፖለቲካው መስክ በስውርና በግልጽ የሃገራትን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚረባረቡበት መስክ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን አያይዘው እንደገለጹት ሃገራችን ከምትገነባው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ብሄራዊ ጥቅሞቻችንን ተጻራሪ ከሆኑ ሃይሎች በተደጋጋሚ የሳይበር ጥቃት እየተሰነዘረ መሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል፡፡ ይህንን ጫና ከሚያቃልሉ ጉዳዮች መካከል ጠንካራ የሳይበር መከላከልና ማምከኛ አቅም መፍጠር እጅግ በጣም ወሳኝ ዘረፍ እንደሆነም አስምረውበታል፡፡

በመሆኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን ቀድሞ በመለየት፣ በማክሸፍና በመቆጣጠር የሃገራችን የሳይበር አቅም ማሳያና የሃገር ኩራት የሆነ ተቋም መሆኑን ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች