የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ሰለሞን ሶካ ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች 1 ሺህ 444 ጊዜ ለሚከበረው ኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸዉ እንዳሉት በመላዉ ህዝ ሙስሊም ዘንድ  በድምቀት የሚከበረው የኢድ-አል አድሀ (አረፋ) በዓል  የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያን በሺ ዘመናት ታሪካችን በብዙ ፈታኝ እና እልህ አስጨራሽ ፈተናዎች ብናልፍም  ለሚገጥሙን ችግሮች እጅ ሳንሰጥ  በትዕግስት በጽናትና በአንድነት ችግሮቻችንን እየተሻገርን ለዚህ ደርሰናል ብለዋል፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን ሀገራችን ላይ  የተለያዩ እልህ አስጨራሽ ፈተናዎች ቢደቀኑም  ዛሬም እንደ ትላንቱ  ለችግሮቻችን ሳንንበረከክ  በጽናት እንደምንሻገር ጥርጥር የለውም  ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

ኢድ-አል አድሀ (አረፋ) የእዝነትየመተሳሰብ እና የመደጋገፍ በዓል ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤የዘንድሮውን በዓል ስናከብር ኢትዮጵያዊያን ከምንታወቅባቸው ድንቅ ሴቶቻችን መሀል የመደጋገፍ በተለይም በፈተና እና በችግር ወቅት የመረዳዳት  ባህላችን መሆኑን ጠቁመዋል። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ከቤት ንብረታቸው እና ከቄያቸው ተፈናቀለው ለሚገኙ ወገኖቻችን ያለንን በማካፈል  አለኝታነታችንን የምናሳይበት መሆን  ይኖርበታል  ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የደስታ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች