የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አገራዊና ፋይዳቸዉ ላቅ ባሉ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት ምክክር አደረጉ

[#if smallImage??]
  [#if smallImage?is_hash]
    [#if smallImage.alt??]
      ${smallImage.alt}
    [/#if]
  [/#if]
[/#if]

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር(ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ጋር በኢመደአ ዋና መስሪያ ቤት ተወያዩ።በዉይይታቸዉ ክቡር ሚንስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያን የዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ እውን ለማድረግ እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ካሉ የቴክኖሎጂ ባለቤትነት ለማረጋገጥ እየሰሩ ካሉ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ስኬት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

አያይዘውም የአገራችንን የዲጂታል ኢኮኖሚ ለማጠናከርና የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እየሰራቸዉ ያሉ ስራዎች አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የጠቆሙት ክቡር ሚንስትሩ ይህንንም ለአገር በሚጠቅም መልኩ ለመስራት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ቁልፉ ጉዳይ በራስ አቅም የሚሰሩ እና የቴክኖሎጂ ባለቤት የሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ አትኩሮ መስራት እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።ኢመደአ እንደ ተቋም አገራዊ የዲጂታል መሰረተ-ልማቶችን በማልማትና የቴክኖሎጂ ባለቤትነት አቅሞችን እየፈጠር መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሰለሞን እነዚህ ስራዎች የዲጂታል ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬት ወሳኝ ሚና እንዳላቸዉ ገልጸዋል።

አገር ያሰበችዉ ሁሉን አቀፍ የልማት ግቦች ለማሳካት ቴክኖሎጂ አንዱና ወሳኝ መሳሪያ በመሆኑን በዉይይቱ ላይ ያነሱት ክቡር አቶ ሰለሞን ሁሉም ተቋም ባለዉ አቅምና ኃላፊነት ልክ ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር መስራት የሚገባዉ ጊዜ አሁን ነዉ ብለዋል። በተለይም እንደ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር ያሉ ተቋማት በታለንት ልማት፣ በስታርታፖች፣ አገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም በመፍጠርና መስል ጉዳዮች በትብብር በመስራት ለአገራችን ልማትና እድገት አስቻይ ሚናዎችን በመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋፆ ማበርከት እንደሚገባ ተቁመዋል።

ከዚህ ባሻገር ወደ ዲጂታል ኢትዩጵያ የምናድርገዉ ጉዞ የሳይበር ደህንነት ስጋትንም ይዞ ይመጣል ያሉት ክቡር አቶ ሰለሞን እንደ ተቋም ሃገራዊ የሳይበር ምህዳሩን ደህንነት በማስጠበቅ ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል።

ከዉይይቱ በኋላ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ በየኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንን እና የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከሉን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።