የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መጥቷል፡፡

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሀገራችንን የሳይበር ደህንነት ለመጠበቅ በፀጥታና የደህንነት ተቋም ላይ በተደረገው ሪፎርም የሳይበር ደህንነትን የማስጠበቅ ሀገራዊ አቅም እያደገ መምጣጡን የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ የቀደሞ ኢንፎርሜሽን ደህንነት ፖሊሲ ጉድለቶችን በማሻሻል የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነትና ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ስኬቶች መመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ በዘርፉ የሰው ሃይል ልማት ማፍራት ላይ ትኩረት የሚያደርግ የክረምት የስልጠና መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተውጣጡ ታዳጊዎች ስልጠናዎችን በመስጠት ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቁልፍ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚቃጡ አደጋዎችን መከላከል የሚችል በቴክኖሎጂ የተደራጀ የሳይበር ክስተት ምላሽ መስጫ ማዕከል መገንባቱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ ከአለም ሀገራት ጋር ትብብርና ቅንጅትን በማሳደግ መረጃን ቀድሞ በማግኘት እና ለሌሎች በማጋራት እድሎችን ማስፋት ተችሏል ብለዋል፡፡

ኮምቲውተርን መሰረት ያደረጉ ማንኛውም አይነት የወንጀል ድርጊቶች ለሚመለከተው የፍትህ አካላት የማቅረብ እንዲሁም ለአገር ደህንነት ስጋት የሆኑ የቴክኖሎጂ እቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ተጋላጭነታቸውን የመፈተሽ እና ፍቃድ የመስጠት ስራ በቴክኖሎጂ ቁጥጥር በማድረግ እንደሚሰራ ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ አክለው ተናግረዋል፡፡

የማህበረሰቡን ንቃተ ህሊና ማሳደግ የሳይበር ጥቃትን ለመከላከል ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ እንደመሆኑ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ተቋማት የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ ስልጠናዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ የሰው ኃይላችን በማሳደግ ረገድ ከሀገር ውስጥ 8 ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብርና በሳይበር ደህንነት ላይ ትኩረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ተቀርጾ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ደረጃ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እየተሠራ ነው ብለዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች