የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ የህዝብ ዉይይት ተካሄደ

[#if smallImage??]
    [#if smallImage?is_hash]
        [#if smallImage.alt??]
            ${smallImage.alt}
        [/#if]
    [/#if]
[/#if]

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ / ነገሪ ሌንጮ መሪነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች የደህንነት ማረጋገጫና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ ላይ የህዝብ ውይይት ተካሂዷል፡፡

ከባለድርሻ አካላት ጋር በነበር የህዝብ ዉይይት መድረክ ላይ ሰለ ረቂቅ አዋጁ አጠቃላይ ገለጻ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት / ትዕግስት ሀሚድ ቀርቧል። / ትግስት ሀሚድ የረቂቅ አዋጁን አስፈላጊነት አስመልክተው ባደረጉት ገለጻ በሀገር ሉዓላዊነት እና በዜጎች ደህንነት ላይ ስጋት የሚፈጥሩ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶችን መቆጣጠር እና ገደብ መጣል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

በቀረበዉ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተለያዩ ተቋማት የመጡና ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸዉ አካላት ጥያቄዎችን አቅርበዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ / ነገሪ ሌንጮ በውይይቱ ላይ እንዳሉት በቀረበው ረቂቅ ላይ ከተሰጡ አስተያየቶች አስፈላጊ መሆናቸው የታመነባቸው ግብዓቶች ተወስደውና ማስተካከያ ተደርጎበት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለምክርቤት ቀርቦ በቀጣይ እንደሚጸድቅ ገልጸዋል፡፡

በውይይት የተሳተፉ የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው አዋጁ ከመዘግየቱ በስተቀር በአስፈላጊነቱ ላይ ተስማምተው በርካታ ገንቢ አስተያየት እና ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን እንደግብአት የሚወሰዱት አዋጁን የሚያዳብሩ ሆነው በጥቂቶቹ ላይ ማብራሪያ በተቋሙ በኢመደአ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች / ትዕግስት ሀሚድ እና አቶ ዳንኔል ጉታ ተሰጥቶባቸዋል።

Asset Publisher


የቅርብ ዜናዎች